Page 45 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 45

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             እሞክር ስለነበር፣ አንድ ቀን ለምን ሲከፉ እንደተባለች ጠየኳት። እርሷም ስትመልስልኝ፣
             መጀመሪያ የተሰጣት ስም ’ሲከፉ መቻል’ እንደነበረ እና ቀደም ሲል በዚህ ስሟ ስትጠራ
             ‘ለአምላክ ይመቻል’ ብላ መመለስ እንደሚጠበቅባት ነገረችኝ። ከጊዜ በኋላ ይኸው ስሟ
             አጥሮ  ሲከፉ  እንደሆነ  ነገረችኝ።  ይህንን  ከሰማሁ  በኋላ  ሌላ  በቅርብ  የማውቀው
             በተመሳሳይ አገልጋይነት ውስጥ የነበረ ሰጠኝ የሚባል ሰው ስለነበር እርሱንም ለምን ሰጠኝ
             እንደተባለ ጠየኩት። እርሱም ሲመልስልኝ፣ ቀደም ሲል የወጣለት ስም ‘ሰጠኝ መርቆ’
             እንደነበር  እና  ይህ  ስሙ  በሚጠራበት  ጊዜ  እርሱም  ‘ልፋቴን  አውቆ’  ብሎ  መመለስ
             ይጠበቅበት እንደነበር አጫወተኝ። ይህ ታሪክ የሚያሳየው፣ በቅርብ ጊዜ ታሪካችን እንኳን
             ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ እንደ ዕቃ የሚመለከት ሥርዓት ብቻ ሳይሆን ይህንን አሳፋሪ
             ሥርዓት በመለኮታዊ አባባል ለማጽዳት (sanitize) ጥረት ይደረግ እንደነበር ነው።
                      ሁለተኛው መዋቅራዊ ችግር የዲሞክራሲ ሥርዓቱን የሚመለከት ሲሆን፣ ባንዱ
             ጫፍ  ያሉ  ወገኖች  የኢትዮጵያ  የዴሞክራሲ  ሥርዓት  አሁን  ሰፍኖ  ካለው  በአብዮታዊ
             ዲሞክራሲ  ከተቃኘው  የብሔር  ፖለቲካ  ተቀይሮ  በሊበራል  ዲሞክራሲ  ቅኝት
             ወደሚመራው  በግለሰብ  ነፃነት  ላይ  ወደ  ተመረኮዘ  የዜግነት  ፖለቲካ  በአስቸኳይ
             ካልተሸጋገረ ሃገሪቱ በማያባራ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትቀጥላለች ብለው ያምናሉ። በሌላ
             በኩል ደግሞ፣ የብሔር ጥያቄ የሀገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ ጥያቄ በመሆኑ፣ የሀገሪቱ የፖለቲካ
             ሥርዓትም በዚሁ ዙሪያ ከመዋቀር ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም ብለው የሚያምኑ ወገኖች
             አሉ።  በተጨባጭ ካለው አለም አቀፍ ተመክሮ እንደምንረዳው በፍጹማዊ የግለሰቦች
             ነፃነት  ላይ  የተመረኮዘ  ዴሞክራሲያዊ  ሥርዓት  ገንብተናል  ብለው  የሚኩራሩ  በርካታ
             የበለፀጉ ሀገሮች በተለያየ ወቅት በሚነሱ የቡድን ጥያቄዎች ሲፈተኑ ኖረዋል ወደፊትም
             ይፈተናሉ።
                     በቅርቡ በአሜሪካ የተነሳው የጥቁር ህዝቦች በህይወት የመኖር መብት ጥያቄ
             በግለሰቦች  መብት  መጠበቅ  ሽፋን፣  ስር  ለሰደዱ  የቡድን  መብት  ጥያቄዎች  ተገቢውን
             ትኩረት ካለመስጠት ጋር የተያያዘ ነው። በኢትዮጵያም ሁኔታ ለረጅም ዘመናት የነበረውን
             የብሔረሰቦች መብት ጥያቄን መመለስ አንዳንዶች እንደሚያስቡት ወደጎን ሊባል የሚችል
             ጉዳይ አይደለም። ነገር ግን፣ ይህንን ጥያቄ ለመመለስ የሚወሰዱ እርምጃዎች በምንም
             አይነት አገባብ የዜጎችን ወይም የግለሰቦችን በህይወት የመኖር፣ የመሳተፍ እና የመበልፀግ
             መብቶችን  የሚገድቡ  ሊሆኑ  አይገባም።  ስለሆነም  የብሔረሰቦችን  መብት  ከዜጎች
             መሰረታዊ መብት ጋር ማጣጣም የወደፊቱ የፖለቲካ ሥርዓታችን ዋነኛ መገለጫ ሊሆን
             ይገባዋል።
                     ከምህዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ፣ በግለሰብ መብት እና ቡድን መብት መካከል
             ጥብቅ የሆነ መተሳሰር ከመኖሩም በላይ ባንዱ ላይ ብቻ የተመረኮዘ የፖለቲካ ሥርዓት
             የተሟላ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ይሆናል ተብሎ አይታመንም። ባላፉት ጥቂት ዓስርተ
             ዓመታት ውስጥ፣ የአብዮታዊ እና ሊበራል ዲምክራሲ ዲቃላነት ባህርይ ያላቸው ‘የልማት
             መንግሥታት’  (developmental  states)፣  ኢትዮጵያን  ጨምሮ  በተለያዩ  ሃገሮች  እንደ
             አማራጭ  ተራምደዋል።  ሆኖም  ግን፣  በሃገራችን  እንደታየው፣  እነኚህ  መንግሥታዊ
                                                                        37
   40   41   42   43   44   45   46   47   48   49   50