Page 50 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 50

ደስታ መብራቱ


           ተዋናይነት ከቀድሞው የዳር መሃል ሃገር ፖለቲካ የቀጠለ መሆኑ ግልጽ ነው። በመሆኑም፣
           ለበርካታ ዓመታት በኢህአዴግ ውስጥ ሰፍኖ የነበረው የትግራይ ህዝቦች ነፃ አውጭ ግንባር
           (ህወሃት)  የበላይነት፣  በዋነኝነት፣  በኦሮሞ  እና  በአማራ  (ኦሮማራ)  የፖለቲካ  ሃይሎች
           ጥምረት ሊፈርስ ችሏል። ይህም የሚያመላክተው፣ በቅርቡ በነበረው የፖለቲካ ዘመናችንም
           ቢሆን ከእነኚህ ሶስት ወገኖች በሚወጡ የፖለቲካ ልሂቃኖች መካከል ያለው መስተጋብር
           የሃገሪቱን የፖለቲካ አቅጣጫ በመወሰን ረገድ ትልቅ ድርሻ እንደነበረው ነው።
                  ይህ የዳር እና የመሃል ሃገር ፖለቲካ፣ ከ2010 የመንግስት አመራር ለውጥ ወዲህ
           እየተሻሻለ መምጣቱን የሚያመላክቱ አንዳንድ በጎ እርምጃዎች መታየት መጀመራቸው
           ግልጽ  ነው።  ያም  ሆኖ፣  የሃገሪቱን  የወደፊት  ፖለቲካ  እጣ  ፈንታ  በመወሰኑ  ረገድ
           በአማራው፣ በአሮሞው እና በትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን መካከል የሚካሄደው የፖለቲካ
           መስተጋብር አሁንም ወሳኝ ድርሻ እንደሚኖረው የሚያምኑ ወገኖች በርካታ ናቸው። ከላይ
           የተጠቀሱት ታሪካዊ ሁኔታዎች የሚያመላክቱት በመግቢያው ላይ የተጠቀሰውን የሃገሪቱን
           የፖለቲካ ችግሮች በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ አብይ ድርሻ ከነበራቸው የሶስቱ
           ብሄረሰቦች  ልሂቃን  ጋር  ያያዘው  አስተያየት  በቂ  መነሻ  መሰረት  እንደነበረው  ነው።
           በመሆኑም፣  በየትኛውም  የሃገሪቱ  ዘመን  ለነበረው  የፖለቲካ  ቀውስ  ከእነኚህ  ሶስት
           ብሔረሰቦች የወጡ የፖለቲካ መሪዎች እና ልሂቃን የጋራ ተወቃሽነት አለባቸው ማለት
           ይቻላል።
                  የእነኚህ  ሶስት  ብሔረሰቦች  ህዝቦች  በሀገሪቱ  የታሪክ፣  ኢኮኖሚ  እና
           መልክዓምድራዊ ይዞታ ውስጥ ካላቸው ጉልህ ድርሻ አኳያ፣ በሃገሪቱ የፖለቲካ ህይወት
           ውስጥ የጎላ ድርሻ መያዝ በራሱ የችግር ምንጭ ሊሆን አይገባውም። ይልቁንም፣ እነኚህ
           ህዝቦች ለሃገሪቱ የረጅም ዘመን ታሪክ ከነበራቸው ጉልህ አስተዋጽኦ እና ካከማቹት ከፍተኛ
           ማህበራዊ ንዋይ (social capital) አኳያ በጣም ጠቃሚ የሆነ የአካታችነት (inclusivity)
           እና የአረጋጊነት (stability) ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። ይህንን ሆኖ ለመገኘት ግን፣ ከዚህ
           ቀጥሎ ከተጠቀሱት ህመሞች ራሳቸውን ማንጻት ይጠበቅባቸዋል።
                  የመጀመሪያው፣ የፖለቲካ ልሂቃኖቹ ለዘመናት ተብትቦ ከያዛቸው በሴራ እና
           እርስ በርስ በመጠፋፋት ላይ ከተመረኮዘ ባላባታዊ ፖለቲካ ራሳቸውን በማንጻት የዳር
           ሃገር ህዝቦችን እኩል ተሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል። በሁለተኛ
           ደረጃ፣ በሃሳብ ልዕልና ላይ ከተመረኮዘ መንግስታዊ ሥርዓት ይልቅ፣ ባላቸው የህዝብ
           ቁጥር ትልቅነት ላይ ወደተመረኮዘ ጨቋኝ አገዛዝ (tyranny of numbers) የሚወስድ
           ዝንባሌን በጥብቅ ሊታገሉ ይገባቸዋል። በአሁኑ ወቅት፣ እንዲህ አይነቱ የፖለቲካ ዝንባሌ
           በዲሞክራሲ ሽፋን በአንዳንድ የብሄር ፖለቲካ ልሂቃን እና መሪዎች አካባቢ እየተቀነቀነ
           በመሆኑ በቶሎ ሊታረም ይገባዋል።
   45   46   47   48   49   50   51   52   53   54   55