Page 55 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 55

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             4. ማንነት እና የዳያስፖራው ፖለቲካ
                     ከማንነት ጋር የተያያዙ የፖለቲካ ጥያቄዎች      በ1960ዎቹ የተማሪዎች ንቅናቄ
             መቀንቀን ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ የፖለቲካ ውዝግብ ምንጮች ነበሩ። ከ1983 የመንግስት
             ለውጥ በኃላ፣ የማንነት ጥያቄ የተለየ ተቋማዊ ቅርጽ እና ይዘት ይዞ በመምጣቱ የሃገሪቱ
             ፖለቲካ ምስቅልቅል ዋነኛ ምንጭ ሊሆን ችሏል። አንዳንዶች በየዋህነት እንደሚያስቡት፣
             የማንነት  ጥያቄ  እንዲህ  በቀላሉ  ገሸሽ  (write-off)  የሚደረግ  ሳይሆን  ባግባቡ
             ልንመለከተው  እና  ልንወያይበት  የሚገባ  ጉዳይ  ነው።  ይህም፣  በሃገራችን  ውስጥ  ያሉ
             መሰረታዊ  የማንነት  ቀውስ  ምንጮችን  መመርመር  እና  ተገቢውን  ምላሽ  መስጠት
             ይጠይቃል።

                                              17
             4.1 የማንነት ቀውስ እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ
                     በህዝቦች  መካከል  ለበርካታ  ምዕተ  ዓመታት  በተለያየ  ደረጃ  የነበሩት
             መስተጋብሮች  እና  መተሳሰሮች  የአሸብራቂው  የኢትዮጵያ  ታሪክ  ዋነኛ  መሰረቶች
             መሆናቸው እሙን ነው። ይህ የህዝቦች መተሳሰር ባለፉት ጥቂት ዓስርተ ዓመታት በሃገሪቱ
             የተከሰቱትን  ከፍተኛ  የፖለቲካ  ምስቅልቅሎች  ለመሻገር  ዓብይ  ድርሻ  የነበረው  እና
             ወደፊትም የሚኖረው መሆኑ አያጠያይቅም። ነገር ግን፣ ይህ በህዝቦች መካካል ለዘመናት
             የቆየው መተሳሰር በዘመናዊቷ ኢትዮጵያ የሃገረ መንግስት ምስረታ ሂደት ውስጥ ክፉኛ
             ተፈትኗል፣ በመፈተንም ላይ ይገኛል። የዚህም ፈተና ዋነኛው አስኳል በሁለት ልዩ ታሪካዊ
             ወቅቶች  በተግባር  ላይ  ከዋሉ  የአሃዳዊነት  ሥርዓቶች  ጋር  በተያያዘ  የተፈጠሩ  የማንነት
             ቀውሶች (Identity crisis) ናቸው።

                     የመጀመሪያው፣  የኢትዮጵያን  ሃገረ  መንግስት  በአንድ  ወጥ  አሃዳዊነት
             (Monocultural unitarianism) ላይ በተመረኮዘ ማንነት ለመገንባት ከተደረገው ጥረት
             ጋር  የሚያያዝ  ሲሆን፤  ሁለተኛው፤  ቀደም  ሲል  በአሃዳዊነት  ዘመን  የደረሰውን  በደል
             ለማከም በሚል በተወሰዱ መንግስታዊ እርምጃዎች የተፈጠረው ብሔረሰባዊ አሃዳዊነት
             (Ethnicised unitarianism) ናቸው። የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለማከም የሚደረገው ጥረት፣
             የእነኚህን የማንነት ቀውሶች ምንጭ ባግባቡ በመረዳት መፍትሄ መሻትን ይጠይቃል። የዚህ
             ክፍል ዋነኛ ትኩረት እነኚህን አበይት የማንነት ቀውሶች ከምህዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ
             በመመርመር  የመፍትሄ ሃሳቦችን መጠቆም ነው።

                     ከዘመነ  መሳፍንት  በኃላ  ኢትዮጵያን  እንደገና  ለማጠናከር  እና  ዘመናዊ  ፈር
             ለማስያዝ በዓጼ ቴዎድሮስ የተጀመረው እና በተከታታይ ነገሥታት የቀጠለው ሂደት በሃገሪቱ
             ታሪክ ውስጥ ለዘመናዊቷ ኢትዮጵያ መመስረት እንደ አዲስ ፈር ቀዳጅ ተደርጎ ይወሰዳል።
             ይህ  የአገዛዝ  ሽግግር፣  ለጥቁር  ህዝቦች  የነፃነት  ተምሳሌት  የሆነውን  የዓድዋን  ድል
             ለማስገኘት  እና  ሃገሪቱንም  ከቅኝ  ተገዢነት  ለመከላከል  ያስቻለውን  ታላቅ  ማህበራዊ


             17  የዚህ ክፍል አብዛኛው፣ ነሐሴ 2 ቀን 2012 በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ታትሟል።
                                                                        47
   50   51   52   53   54   55   56   57   58   59   60