Page 57 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 57

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     ከዚህ  ውስጥ  አንዱ  መገለጫ፣  በርካታ  የእስልምና  እምነት  ተከታይ  የሆኑ
             ተማሪዎች  ባሉበት  ትምህርት  ቤት  ውስጥ  በየዕለቱ  ጠዋት  ትምህርት  ከመጀመሩ  በፊት
                                                   18
             የክርስትያኑን ፀሎት ሁሉም እንዲጸልዩ ማስገደድ ነበር ። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ በልጅነት
             አእምሮዬ ከሚያሳዝኑኝ ትውስታዎቼ አንዱ የተወሰኑ አብሮ አደግ ጓደኞቼ በረመዳን ጾም
             ወቅት ይህንን የግዴታ ፀሎት ላለመጸለይ ሲሉ ዘግይተው ወደ ትምህርት ቤት በመምጣት
             ወደ ክፍል ከመግባታቸው በፊት የሚደርስባቸው ቅጣት ነበር። ከላይ የቀረቡት ምሳሌዎች
             በእኛው  ዘመን  ከነበረው  ታሪካችን  እንደማሳያ  የቀረቡ  ሲሆኑ  ከዚህም  የከፉ  በርካታ
             የአሃዳዊነት መገለጫዎች ተቋማዊ በሆነ ደረጃ ይራመዱ እንደነበር መካድ ራስን መሸንገል
             ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ በርካታ ወገኖቻችን በተለያየ መልክ ለሚገለጹ የማንነት ቀውሶች
             እንዲጋለጡ እና አንዳንድ ወገኖችንም ኢትዮጵያዊነታቸውን እስከመጠራጠር እንዲደርሱ
             አድርጓቸዋል።

                     የዘመናዊ ትምህርት በሃገሪቱ እየተስፋፋ መምጣቱ እና ከፊውዳላዊው ሥርዓት
             ጋር ተያይዞ ከነበረው መጠነ ሰፊ ጭቆና ጋር መጣጣም አለመቻሉ ለተማሪው እንቅስቃሴ
             መጀመር  ዋነኛ  ምክንያት  ነበር።  ከዚህ  በተጨማሪ፣  ከላይ  በተጠቀሰው  አሃዳዊ  አገዛዝ
             ምክንያት ተፈጥሮ የነበረው የማንነት ቀውስ የተለያዩ የማንነት መብት ጥያቄዎች እንዲነሱ
             አድርጓል።   በመሆኑም፣ በርካታው ተማሪ መሰረታዊ የሆኑ ሃገራዊ እና ሰብአዊ የመብት
             ጥያቄዎችን  እንደሃገራዊ  ዋነኛ  የለውጥ  መታገያ  ሲያነሳ፣  የተወስኑት  ደግሞ  የብሄረሰቦች
             የራስን  ዕድል  በራስ  የመወሰን  መብት  እንደዋነኛ  መታገያ  ሊያነሱ  ችለዋል።  የተማሪው
             ንቅናቄ ድርጅታዊ ቅርጽ እየያዘ ሲመጣም፣ የመጀመሪያዎቹ ወደ ህብረ ብሄራዊ የፖለቲካ
             ድርጅትነት ሲቀየሩ ሁለተኞቹ ደግሞ ወደ ብሔረሰብ ነፃ አውጪ ድርጅትነት ተሸጋገሩ።

                     የየካቲት 1966 የህዝብ ንቅናቄን ተከትሎ፣ ወታደራዊው ደርግ አንዳንድ የጭቆና
             መገለጫዎችን ለማስወገድ የሚያስችሉ እርምጃዎችን የወሰደ ቢሆንም፣ መሰረታዊ ሃገራዊ
             አንድነትን ለማምጣት የሚያስችሉ መብቶችን ሊያከብር አልቻለም። ከዚህ ይልቅ፣ በወቅቱ
             የነበሩት የፖለቲካ ድርጅቶች የነበረባቸውን ድክመት በመጠቀም የራሱን አምባገነናዊ አገዛዝ
             ለማጠናከር በወሰደው እርምጃ ለበርካታ ብርቅዬ ዜጎች መሰዋት ምክንያት ሆኗል። በዚህ
             እርምጃው፣ ወታደራዊው ደርግ በቀዳሚነት ለማጥፋት ቆርጦ የተነሳው በፍጹም የሃገር እና
             የህዝብ  መውደድ  ስሜት  በተለያዩ  ህብረ  ብሄራዊ  የፖለቲካ  ድርጅቶች  ስር  ተሰባስበው
             ይታገሉ የነበሩትን መሆኑ የሃገሪቱን ቀጣይ ዘመን እጅግ ፈታኝ አድርጎታል። ይህ ሁኔታም፣
             በዋነኝነት የብሔር ጭቆናን ለመታገል በሚል የተደራጁት የብሔር ነጻ አውጪ ድርጅቶች
             ይበልጥ እንዲጠናከሩ እና ሰፊ ማህበራዊ መሰረት እንዲያገኙ አግዟቸዋል። የኢትዮጵያ
             ህዝብ አብዮታዊ ሠራዊት (ኢህአሠ) መበተን እና የህወሃት ተጠናክሮ መውጣት ከዚህ
             ሁኔታ ጋር የተያያዘ እንደነበር ይነገራል።



             18  ይህ ሁኔታ፣ በወቅቱ እንደወሎ እና ሐረርጌ ክፍለ ሃገር ከነበሩ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች
             በስተቀር  በአብዛኛዎቹ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤቶች የነበረ እውነታ ነው።
                                                                        49
   52   53   54   55   56   57   58   59   60   61   62