Page 53 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 53

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     (consensus) ላይ የተመረኮዘ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገንባት አጅግ አስፈላጊ
                     ይሆናል።
               iv.   ሶስተኛው መዋቅራዊ ፈተና፣ አሁን በስራ ላይ ካለው ህገመንግስት ጋር የተያያዘ
                     ነው። ይህን በተመለከተ፣ ባንድ በኩል አሁን ያለው ህገመንግስት በመሰረታዊ
                     ባህሪው ኢዴሞክራሲያዊ በመሆኑ ሙሉ በሙሉ ማስወገድ እና በሌላ አዲስ
                     ህገመንግስት መተካት አለበት ብለው የሚያምኑ ወገኖች አሉ። በሌላ በኩል
                     ደግሞ፣  ይህ  ህገመንግስት  የብሔረሰቦችን  መብት  ያስከበረ  በመሆኑ  እርሱን
                     ለመቀየር መሞከር ሃገሪቱን ወደ መበታተን ሊወስዳት ይችላል የሚሉ ወገኖች
                     አሉ። ከምህዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ፣ የትኛውም ህገመንግስት ከጅምሩ ሙሉ
                     በኩለሄ  ሆኖ  የሚፈጠር  ሳይሆን  በየወቅቱ  እየተሻሻለ  እና  እየበለፀገ  የሚሄድ
                     ህልው (organic) ሰነድ ነው።
                v.   አራተኛው ፈተና፣ በስራ ላይ ካለው ህገመንግስት ጋር በተያያዘ ሃገሪቱ ሊኖራት
                     የሚገባው የፌዴራል አወቃቀርን ይመለከታል። ባንድ በኩል፣ አሁን በስራ ላይ
                     ያለው  በብሔር  ላይ  የተመረኮዘ  የፌደራል  መዋቅር  የሃገሪቱን  አንድነት
                     የሚፈታተን እና ወደመበታተን የሚያመራ ስለሆነ ሙሉ በሙሉ መቀየር አለበት
                     ብለው የሚያምኑ ወገኖች አሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ ያለው የፌደራል አወቃቀር
                     ለብሔሮች ራስን በራስ የማስተዳደር መብት ያጎናጸፈ በመሆኑ እርሱን ለመቀየር
                     መሞከር  ሀገሪቱን  ወደ  ብጥብጥ  እና  መበታተን  ሊወስዳት  ይችላል  የሚሉ
                     ወገኖች  አሉ።   ከምህዳራዊው  አስተሳሰብ  አኳያ፣  የማንኛውም  ፌደራላዊ
                     ሥርዓት  ውጤታማነት  የሚለካው  ማንኛውም  ሰው  በሰውነቱ  ሊኖረው
                     የሚገባውን መሰረታዊ የመኖር እና በአካልም በመንፈስም የመበልፀግ መብቶች
                     ከቡድናዊ መብቶች ጋር አጣጥሞ መተግበር ሲችል ነው።
               vi.   በኢትዮጵያ  የፖለቲካ  ስርዓት  ውስጥ  ዋነኛ  ተዋንያን  ነን  የሚሉ  የፖለቲካ
                     ፓርቲዎች የአጠቃላይ የሃገሪቱ የፖለቲካ ምህዳር አካል ናቸው። ይህም ማለት፣
                     አንዱ ፓርቲ ከሌላው ፓርቲ ጋር የሚኖረው መስተጋብር ባጠቃላይ የምህዳሩን
                     ጤናማነት ይወስነዋል። በመሆኑም በማንኛውም ወቅት ለሚፈጠር የፖለቲካ
                     ቀውስ፣ (የድርሻ ማነስ ወይም መብዛት ካልሆነ በስተቀር) የትኛውም ፓርቲ
                     ከደሙ ንጹህ ነኝ ማለት አይችልም። ከዚህ አኳያ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች ቀዳሚ
                     ተግባር  መሆን  ያለበት  ለህዝቦች  ልዕልና  ተገዢ  በመሆን፤  ዋነኛ  የሆኑት
                     መዋቅራዊ የፖለቲካ ችግሮችን እውቀት ላይ በተመረኮዘ አካሄድ በሂደት ሊፈቱ
                     የሚችሉበትን መንገድ  ማዘጋጀት እና መተግበር ነው።
               vii.   በርካታ  ኢትዮጵያውያን  ‘የኢትዮጵያ  ፖለቲካ  ዋነኛው  ችግር  በአማራው፣
                     በኦሮሞው እና በትግራይ የፖለቲካ ልሂቃን (elites) መካከል ያለው የበላይነት
                     ፉክክር ነው’ የሚል እምነት አላቸው። እነኚህ አስተያየቶች በሃገራችን ፖለቲካ
                     ውስጥ ካሉት እና ትኩረት ሊሰጣቸው ከሚገቡ ዋነኛ መዋቅራዊ ችግሮች አንዱ
                     የሆነውን  የመሃል  እና  ዳር  (centre-periphery) ፖለቲካን  የሚያመላከቱ
                     ናቸው። ይህ የዳር እና የመሃል ፖለቲካ በረጅሙ የመሳፍንት ዘመን መሰረቱን

                                                                        45
   48   49   50   51   52   53   54   55   56   57   58