Page 52 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 52

ደስታ መብራቱ


                  ባለፉት ሁለት የሽግግር ዓመታት ውስጥ፣ በአፋር እና በሶማሊ ክልሎች የታየው
           አንጻራዊ  መረጋጋት  እና  ሰላም  ለሃገሪቱ  ቀጣይነት  የነበረው  አስተዋጽኦ  ለዚህ  አንድ
           ማረጋገጫ  ይሆናል።  ከዚህ  በተጨማሪ፣  የአንድ  የፖለቲካ  ሥርዓት  ዴሞክራሲያዊነት
           ከሚመዘንበት ዋነኛ የመልካም አስተዳደር መስፈርቶች አንዱ ለአናሳ የማህበረሰብ ክፍሎች
           በሚሰጠው  የመብት  ጥበቃ  መሆኑን  የፖለቲካ  መሪዎቻችን  ተረድተው  ዳሩን  ከመሃሉ
           ለሚያስተሳስር ፖለቲካ መትጋት ይኖርባቸዋል። በሌላ በኩል ደግሞ፣ በእነኚህ ክልሎችም
           የሚገኙ ወጣት የፖለቲካ መሪዎች እየተካሄደ ላለው ሽግግር ልዩ እና ጠቃሚ አስተዋጽኦ
           ሊያደርጉ የሚችሉበት ታሪካዊ ወቅት ላይ መሆናቸውን ተገንዝበው ለሃገራዊው አንድነት
           ምስረታ ድርሻቸውን አጠናክረው ማበርከት ይጠበቅባቸዋል።

           የክፍል ሶስት ቁልፍ ሐሳቦች
              i.   ከመዋቅራዊ ችግሮቻችን የመጀመሪያው፣ በሃገራችን ታሪክ ላይ ያለው ሁለት
                  ጽንፍ የያዘ አመለካከት ነው። ባንደኛው ጽንፍ፣ ኢትዮጵያ ቀደምት እና እጅግ
                  አኩሪ የሆነ ታሪክ ያላት አገር ናት በማለት ሲያምን በሌላኛው ጫፍ ደግሞ፣
                  ኢትዮጵያ የምትባለው ሃገር ከአንድ መቶ ሃያ ወይም ሰላሳ ዓመት ወዲህ በነበሩ
                  ወረራዎች የተፈጠረች እና ታሪኳም የህዝቦች ጭቆና እና ግፍ ታሪክ ነው የሚል
                  ነው።  ከምህዳራዊ  አስተሳሰብ  አኳያ፣  እንደብዙዎቹ  ሃገሮች  ኢትዮጵያም
                  አንፀባራቂ እና አሳፋሪ የታሪክ ምዕራፍ አሳልፋለች። በመሆኑም፣ ያለን ብቸኛው
                  እና ጠቃሚው መንገድ ከዚህ የታሪክ ዕውነታ በመማር በአኩሪ እና ጠቃሚው
                  ላይ መገንባት እና አሳፋሪው እና ጎጂው እንዳይደገም መጣር ነው።
             ii.   ሁለተኛው መዋቅራዊ ችግር የዴሞክራሲ ሥርዓቱን የሚመለከት ሲሆን፣ ባንዱ
                  ጫፍ ያሉ ወገኖች የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሥርዓት አሁን ሰፍኖ ካለው የብሔር
                  ፖለቲካ  ተቀይሮ  በግለሰብ  ነፃነት  ላይ  ወደ  ተመረኮዘ  የዜግነት  ፖለቲካ
                  በአስቸኳይ ካልተሸጋገረ ሃገሪቱ በማያባራ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ትቀጥላለች
                  ብለው ያምናሉ። በሌላ በኩል ደግሞ፣ የብሔር ጥያቄ የሀገሪቱ ዋነኛ የፖለቲካ
                  ጥያቄ በመሆኑ የሀገሪቱ የፖለቲካ ሥርዓትም በዚሁ ዙሪያ ከመዋቀር ውጭ ሌላ
                  አማራጭ  የለውም  ብለው  የሚያምኑ  ወገኖች  አሉ።  ከምህዳራዊ  አስተሳሰብ
                  አኳያ፣  በግለሰብ  መብት  እና  ቡድን  መብት  መካከል  ጥብቅ  የሆነ መተሳሰር
                  ከመኖሩም  በላይ  ባንዱ  ላይ  ብቻ  የተመረኮዘ  የፖለቲካ  ሥርዓት  የተሟላ
                  ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ይሆናል ተብሎ አይታመንም።
             iii.   ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን ይዞት ከመጣው በርካታ ፈተናዎች እና እድሎች
                  አኳያ አብዮታዊ ዲሞክራሲም ሆነ ሊበራል ዲሞክራሲ ዘመኑን የማይመጥኑ
                  መሆናቸው  ይነገራል።  ለምሳሌም  ያህል፣  የመረጃ  እና  ግንኙነት  ቴክኖሎጂ
                  በፈጠረው አመቺነት ላይ በመመርኮዝ ህዝቦች በመንግስታዊ ፖሊሲ ውሳኔዎች
                  ላይ የሚኖራቸው ቀጥተኛ ተሳታፊነት (e-Governance) እያደገ እንደሚሄድ
                  ይጠበቃል።  ከዚህም  በላይ፣  አካታች  እና  ዘላቂ  ልማት  ለማረጋገጥ
                  ከምንጊዜውም  የበለጠ  አሳታፊ  (participatory)  እና  በሰፊ  መግባባት
   47   48   49   50   51   52   53   54   55   56   57