Page 54 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 54
ደስታ መብራቱ
የጣለ ቢሆንም በተከታታይ የነበሩ መንግስታትም መልኩን በመጠኑ ከመቀየር
ባለፈ መሰረታዊ ይዘቱን አልቀየሩትም።
viii. ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ በዘመነ ኢህአዴግ በአንድ በኩል ሁሉም ህዝቦች ራሳቸውን
በራሳቸው የሚያስተዳድሩበት እና የራሳቸውን እድል በራሳቸው የሚወስኑበት
ህገ መንግስታዊ ሥርዓት በመመስረት ህዝቦች በእኩልነት የሚሳተፉበት ሥርዓተ
መንግስት እንደተተገበረ ሲነገር ቆይቷል። በሌላ በኩል ግን፣ በፌደራል ደረጃ
ወሳኝ የሆነውን የፓርቲም ሆነ መንግስታዊ ስልጣን በሚመለከት በቀድሞው
አጠራር ዳር ሃገር፣ በኢህአዴግ አጠራር ታዳጊ ክልሎች የሚባሉትን ህዝቦችን
በአግባቡ ያላካተተ እንደነበር ይታወቃል።
ix. ከምህዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ፣ የአማራ፣ የኦሮሞ እና የትግራይ ህዝቦች በሀገሪቱ
የፖለቲካ ህይወት ጉልህ ድርሻ መያዝ በራሱ የችግር ምንጭ ሊሆን አይገባውም።
ይልቁንም፣ እነኚህ ህዝቦች ለሃገሪቱ የረጅም ዘመን ታሪክ ከነበራቸው ጉልህ
አስተዋጽኦ እና ካበለጸጉት ከፍተኛ ማህበራዊ ንዋይ (social capital) አኳያ
በጣም ጠቃሚ የሆነ የአካታችነት (inclusivity) እና የአረጋጊነት (stability)
ሚና ሊጫወቱ ይችላሉ። ይህንን ሆኖ ለመገኘት ግን፣ ከዚህ ቀጥሎ ከተጠቀሱት
ህመሞች ራሳቸውን ማንጻት ይጠበቅባቸዋል።
x. የመጀመሪያው፣ የፖለቲካ ልሂቃኖቹ ለዘመናት ተብትቦ ከያዛቸው በሴራ እና
እርስ በርስ በመጠፋፋት ላይ ከተመረኮዘ ባላባታዊ ፖለቲካ ራሳቸውን ማንጻት
ይኖርባቸዋል። በሁለተኛ ደረጃ፣ በሃሳብ ልዕልና ላይ ከተመረኮዘ መንግስታዊ
ሥርዓት ይልቅ ባላቸው የህዝብ ቁጥር ትልቅነት ላይ ወደተመረኮዘ ጨቋኝ
አገዛዝ (tyranny of numbers) የሚወስድ ዝንባሌን በጥብቅ ሊታገሉ
ይገባቸዋል። በሶስተኛ ደረጃ፣ በጠረፍ አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ለኢትዮጵያ ዳር
ድንበር መከበር እና ለሃገራዊ እሴት ግንባታ ቁልፍ አስተዋጽ ማበርከታቸውን
መረዳት ነው።