Page 49 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 49

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             የፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም አውራጃ ገዢነት ሹመቶች ይጠቀሳሉ። ስለሆነም፣ በዚህ
             ዘመን ወደ ዳር ሃገር መሾም ማለት ንጉሣዊ ግዞተኝነት ተደርጎ ይወሰድ ነበር።

                     የ1966 ህዝባዊ ንቅናቄን ተከትሎ የነበረውን ፖለቲካ በሁለት ዘርፍ መመልከት
             ይቻላል።  አንደኛው  ገጽታ፣  ሃገሪቱን  የመምራት  ስልጣንን  ጠቅልሎ  የወሰደው
             ወታደራዊው ደርግ የነበረው ያስተዳደር እና አመራር ብሄረሰባዊ ተዋጽኦ ሲሆን፤ ሌላው
             በወቅቱ የሃገሪቱ ፖለቲካ ውስጥ ቀዳሚ የነበሩት የፖለቲካ ድርጅቶች የነበራቸው የአመራር
             ስብጥር ነው። የወታደራዊው ደርግን ስብጥር ስንመለከት፣ ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል
             መልኩ ከነኚሁ ሶስት ዋነኛ ብሄረሰቦች የተውጣጡ መሆናቸው ግልጽ ነው። ይህ ሁኔታ
             በወቅቱ የነበረው የሃገሪቱ የመከላከያ ሰራዊት ስብጥር በአብዛኛው ከነኚሁ ብሄረሰቦች
             የተገኘ ከመሆኑ አኳያ ሲታይ ብዙም የሚያስገርም አይሆንም።
                     በጊዜው  የነበሩትን  የፖለቲካ  ድርጅቶችንም  ስንመለከት፣  የሌሎች  አናሳ
             ብሄረሰቦችን ትግል ለማስተባበር በሚል ከተመሰረተው የኢትዮጵያ ጭቁኖች አብዮታዊ
                         16
             ትግል (ኢጭአት ) ከሚባለው ድርጅት በስተቀር ያብዛኛዎቹ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች
             አመራሮች  ከነዚሁ  ሶስት  ብሄረሰቦች  የወጡ  መሆናቸው  ይታወቃል።  ከዚህም  አልፎ
             አንዳንዶቹ ላንዱ ወይም ለሌላው ወገን በማድላት ሲታሙም ነበር። ለምሳሌ፣ የመላው
             ኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መኢሶን) የሚባለው ድርጅት ለኦሮሞው በማድላት ሲታማ፣
             የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ (ኢህአፓ) አመራርም በአማራ እና በትግራይ ልጆች
             ተጽአኖ ስር ነው ይባል ነበር። ምንም እንኳን፣ የመኢሶንም ሆነ የኢህአፓ መሪዎች ላንዱ
             ወይንም ለሌላው ብሔረሰብ በተናጠል ለማድላታቸው ቀጥተኛ ማረጋገጫ ባይኖርም፣
             ከላይ የቀረበው አጭር ትንታኔ የሚያሳየው በንጉሱም ሆነ በደርግ ዘመን በነበረው የሃገሪቱ
             ፖለቲካ ሥርዓት ውስጥ፣ ከላይ ከተጠቀሱት ሶስት ማህበረሰቦች የወጡ ልሂቃን ወሳኙን
             ድርሻ ይዘው እንደነበር ነው።

                     ይህ የዳር‐መሀል ሃገር ፖለቲካ በዘመነ ኢህአዴግ ለየት ያለ መልክ ይዞ ቀጥሏል።
             በአንድ በኩል፣ ሁሉም ህዝቦች ራሳቸውን በራሳቸው የሚያስተድድሩብት እና የራሳቸውን
             እድል በራሳቸው የሚወስኑበት ህገ መንግስታዊ ሥርዓት በመመስረት ህዝቦች በእኩልነት
             የሚሳተፉበት  ሥርዓተ  መንግስት  እንደተተገበረ  ሲነገር  ቆይቷል።  በሌላ  በኩል  ግን፣
             በፌደራል  ደረጃ  ወሳኝ  የሆነውን  የፓርቲም  ሆነ  መንግስታዊ  ስልጣን  በሚመለከት
             በቀድሞው አጠራር ዳር ሃገር፣ በኢህአዴግ አጠራር ታዳጊ ክልሎች የሚባሉትን የአፋር፣
             የሱማሌ፣ የጋምቤላ እና የቤኒሻንጉል ህዝቦችን በአግባቡ ያላካተተ እንደነበር ይታወቃል።
             ከዚህ አለፍ በማለትም፣ በእነኚህ ክልሎች የነበረው ውስጣዊ አስተዳደርም እስከቅርብ ጊዜ
             ድረስ  ከማዕከል  በሚመደቡ  ሞግዚቶች  ይወሰን  እንደነበር  ተነግሯል።  በጥቅሉ፣
             በኢህአዴግ ዘመን የነበረው መንግስታዊ አስተዳደርም በሶስቱ ብሄረሰቦች ዋነኛ የፖለቲካ


             16  የዚህ ድርጅት መሪ ከነበሩት ፖለቲከኞች መካከል በጽኑ ኢትዮጵያዊነቱ የሚታወቀው አቶ
             አሰፋ ጫቦ በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል።
                                                                        41
   44   45   46   47   48   49   50   51   52   53   54