Page 61 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 61

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                                            20
             4.2 ዳያስፖራው እና የኢትዮጵያ ፖለቲካ
                     በአንድ ወቅት፣ ካንድ ወዳጄ ጋር ኢትዮጵያውያኖች ከሃገራችን ውጪ ስንኖር
             ከኢትዮጵያዊነታችን ጋር ያለንን ማህበራዊ ትስስር ለማቆየት የምንሄድበትን ርቀት ከሌሎች
             የአፍሪካ  ሃገራት  ዜጎች  ጋር  እያወዳደርን  በመገረም  ተወያይተን  ነበር።  በዚህ  ውይይት
             የደረስንበት  ማጠቃለያ፣  በርግጥም  እንደሚባለው  ‘ኢትዮጵያዊውን  በአካል  ከኢትዮጵያ
             ታወጣው  እንደሆነ  እንጂ  ኢትዮጵያን  ከኢትዮጵያዊው  ውስጥ  ማውጣት  እንደማይቻል
             ነበር’። ይህም፣ የሃገሪቱ ህዝቦች ካሏቸው ጥልቅ ማህበራዊ እና ታሪካዊ መሰረት ጋር የተያያዘ
             መሆኑ  አያጠያይቅም።      ከዚሁ  ጥብቅ  ትስስር  ጋር  በተያያዘ፣  ከሃገር  ውጭ  የሚኖሩ
             ኢትዮጵያውያን በተለያየ ወቅት በሃገሪቱ በተከሰቱ አበይት የፖለቲካ ሁነቶችም ንቁ ተሳታፊ
             እንደነበሩ  ይታወቃል።  ስለሆነም፣  የኢትዮጵያ  ፖለቲካ  ሲነሳ፣  በውጭ  ሃገራት  የሚኖሩ
             ኢትዮጵያውያን የነበራቸውን ጠቃሚም ሆነ ጎጂ አስተዋጽኦዎች አለማንሳት አይቻልም።
             ከሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳዎቹ ወዲህ ያለውን የኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ የፖለቲካ ተሳትፎ
             በምንመለከትበት ጊዜ በዋነኝነት በሚከተሉት ሶስት የዳያስፖራ ፖለቲካ ዘመኖች የሚካተቱ
             ይሆናል።

                     የመጀመርያው፣  ከ1966 የህዝብ  ንቅናቄ  ጋር  በተያያዘ  ከንቅናቄው  በፊት  እና
             በኋላ በነበሩ በርካታ ክስተቶች ውስጥ ከሃገራችን ውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ምሁራን
             እና  ተማሪዎች  የነበራቸው የመሪነት  እና  ተሳታፊነት  ሚና ነው።  የየካቲት ስልሳ  ስድስቱ
             የህዝብ  ንቅናቄ  በተማሪው  እንቅስቃሴ  ውስጥ  ተጸንሶ  በመምህራኑ፣  በታክሲ  ነጂው፣
             በእስልምና እምነት ተከታዩ፣ እና በመለዮ ለባሹ የመብት ጥያቄዎች በመታገዝ ህዝባዊ ንቅናቄ
                           21
             ለመሆን የበቃ ነበር ። ለንቅናቄው መከሰት አብይ ድርሻ ከነበረው የሃገር ውስጥ የተማሪ
             ንቅናቄ በተጨማሪ በሰሜን አሜሪካ እና በአውሮፓ የነበረው የኢትዮጵያውያን ተማሪዎች
             ማህበር የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፋንታ በመወሰን ረገድ ጉልህ ድርሻ ነበረው። ይህ በውጭ
             ሃገር በሚገኙ ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች ይካሄድ የነበረ እንቅስቃሴ በፍጹም የሃገር እና
             ህዝብ  የመውደድ  ስሜት  ላይ  የተመረኮዘ  ቢሆንም፣  ገና  ከጅምሩ  ትግሉ  ሊከተለው
             በሚገባው  አቅጣጫ  ላይ  የተወሰነ  የአካሄድ  ልዩነት  ነበረው።  ይህንን  የአካሄድ  ልዩነት
             ለማስታረቅ እና ለማስማማት የሚያስችል የርዕዮተ ዓለም እና የግብ መመሳሰል ቢኖርም፤
             ጥቂት  መሪዎች  ባሳዩት  የ‘አልሽነፍም  ባይነት‘  አመለካከት  የተነሳ  አንዱ  የሌላውን  ሃሳብ
             ለማዳመጥ  እና  ለማስተናገድ  ዝግጁ  ባለመሆኑ  ክፍተቱ  እየሰፋ  መጠላለፉም  እየባሰበት
             ሊሄድ ችሏል።




             20  የዚህ ክፍል አብዛኛው፣ ነሐሴ 9 ቀን 2012 በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ታትሟል።
             21  ከዚህ ቀደም ሲል፣ በጎጃም፣ በባሌ እና በትግራይ የተነሱ የገበሬዎች እንቅስቃሴዎች ቢኖሩም
             በተወሰደባቸው ወታደራዊ እርምጃ ለህዝባዊ ንቅናቄነት ሳይበቁ ቀርተዋል።
                                                                        53
   56   57   58   59   60   61   62   63   64   65   66