Page 65 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 65

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     በዚህ ረገድ፣ የዛሬዎቹም ሆኑ የወደፊቶቹ የዳያስፖራ ፖለቲካ       አራማጆች እና
             አቀንቃኞች ለራሳቸው ከሚሰጡት የገዘፈ የመሪነት ማማ (pedestal) ወርደው ሃገራዊ
             ለውጡን ወደፊት ለማራመድ በሚያስችሉ ድጋፎች ላይ ቢያተኩሩ የሺህ ዘጠኝ መቶ ስልሳ
             ስድስቱ የዳያስፖራ ትውልድ ፖለቲካ መሪዎች ካጋጠማቸው የታሪክ ተወቃሽነት ሊድኑ
             ይችላሉ።

                     ሁለተኛው፣ ለሃገሪቱ ለውጥ ታላቅ ድጋፍ እና አበርክቶት ሊያረግ የሚችለው
             ዝምተኛው ብዙሃን በጋራም ሆነ በተናጠል እራሱ ሊኖረው የሚችለውን ሚና አሳንሶ ማየቱ
             ነው። በዚህም የተነሳ፣ የበርካታው ዳያስፖራ ኢትዮጵያዊ በጎ ፈቃድ የጥቂት ብልጣብልጥ
                                           24
             ፖለቲከኞች  እና  የማህበራዊ  ሚድያው   አርበኞች  መጠቀሚያ  ሲሆን  ይታያል።
             እንደሚታውቀው፣ ‘በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ እጅግ አሳዛኝ እና አሳፋሪ ሁነቶች በዋነኝነት
             የተከሰቱት  እኩይ  አመለካከት  ባላቸው  ጥቂቶች  ጥንካሬ  ሳይሆን  መልካም  አስተሳሰብ
             ባላቸው ብዙሃኖች ዝምታ ነው’ ይባላል። በቅርቡ በሃገራችን ለደረሰው እና እየደረሰ ላለው
             አሳዛኝ እና አሳፋሪ ኢሰብዓዊ ወንጀል የባላባታዊ ሴራ ፖለቲካ አራማጆች እና ጥቂት ጽንፈኛ
             አመለካከት ያላቸው የማህበራዊ ሚዲያ አርበኞች ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱ ቢሆንም
             የእነኚህን አጥፊ ወገኖችን ተግባር በዝምታ ያስተናገድነው ብዙሃንም የራሳችን ድርሻ አለን።
             በዚህ  ረገድ፣  እነኚህ  የጥፋት  መልእክተኞች  ያላቸውን  መልካም  አጋጣሚ  እና  ዕድል
             በመጠቀም  በህዝቦች  መካከል  መቃቃር  እና  ግጭትን  ለመፍጠር  የሚችሉበትን  ሁኔታ
             ማጥበብ እና ማስወገድ ያስፈልጋል።
                     የሃገራችን ፖለቲካ ለረጅም ጊዜ በጥቂት ጯሂዎች ሲታመስ ቆይቶ ዛሬ ያለንበት
             አሳዛኝም ተስፋ ሰጪም ሁኔታ ላይ ደርሷል። በተለያዩ አገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎች
             የተነሳ፣ አሁን ሃገሪቱ ያለችበት ሁኔታ ከዚህ ቀደም ከነበሩት የሽግግር ወቅቶች እጅግ የተለየ
             መሆኑን መረዳት ያስፈልጋል። በዚህ ጸሃፊ እምነት፣ በሚመጡት ጥቂት ዓመታት በሀገሪቱ
             የሚከሰቱት የፖለቲካ ሁኔታዎች ይህች ሃገራችንን ወይ ወደ ከፍተኛ የልማት እና እድገት
             አቅጣጫ  ይወስዳታል  አለበለዚያ  እንደ  ሃገር  የማትቀጥልበት  ሁኔታ  ውስጥ  ይከታታል።
             ስለሆነም፣ የዚህች ሃገር የነገ እጣ ፋንታ የሚያስጨንቀን ወገኖች ዝምታችንን ሰብረን ባለን
             እውቀት  እና  አቅም  እየተካሄደ  ያለው  ለውጥ  ሁሉንም  አካታች  ወደሆነ  እና  የዜጎችን
             ሁለንተናዊ የዲሞክራሲ እና የልማት ፍላጎቶችን ሊያሟላ ወደሚችል ሥርዓት እንዲሽጋገር
             ማገዝ ይኖርብናል።






             24  በአሁኑ ወቅት፣ ማህበራዊ ሚዲያው በዓለም ዙሪያ ህዝበኝነት (populist) ለሚያጠቃቸው
             ፖለቲከኞች እና ቡድኖች መጠቀሚያ ከመሆን ባሻገር ከፍተኛ ጥፋት ሊያስከትሉ የሚችሉ አክራሪ
             ብሔርተኞች (ultra nationalist) እንዲፈለፈሉ አመቺ ሁኔታ በመፍጠር ላይ ይገኛል።
                                                                        57
   60   61   62   63   64   65   66   67   68   69   70