Page 66 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 66

ደስታ መብራቱ


           የክፍል አራት ቁልፍ ሐሳቦች
              i.   በህዝቦች  መካከል  ለበርካታ  ምዕተ  ዓመታት  በተለያየ  ደረጃ  የነበሩት
                  መስተጋብሮች እና መተሳሰሮች የአሸብራቂው የኢትዮጵያ ታሪክ ዋነኛ መሰረቶች
                  መሆናቸው  እሙን  ነው።  ይህ  የህዝቦች  መተሳሰር  ባለፉት  ጥቂት  ዓስርተ
                  ዓመታት በሃገሪቱ የተከሰቱትን ከፍተኛ የፖለቲካ ምስቅልቅሎች ለመሻገር ዓብይ
                  ድርሻ የነበረው እና ወደፊትም የሚኖረው መሆኑ አያጠያይቅም። ነገር ግን፣ ይህ
                  በህዝቦች መካካል ለዘመናት የቆየው መተሳሰር በዘመናዊቷ  ኢትዮጵያ የሃገረ
                  መንግስት ምስረታ ሂደት ውስጥ ክፉኛ ተፈትኗል፣ በመፈተንም ላይ ይገኛል።
                  የዚህም ፈተና ዋነኛው አስኳል በሁለት ልዩ ታሪካዊ ወቅቶች በተግባር ላይ
                  ከዋሉ  የአሃዳዊነት  ሥርዓቶች  ጋር  በተያያዘ  የተፈጠሩ  የማንነት  ቀውሶች
                  (Identity crises) ናቸው።
             ii.   የመጀመሪያው፣  የኢትዮጵያን  ሃገረ  መንግስት  በአንድ  ወጥ  አሃዳዊነት
                  (Monocultural  unitarianism)  ላይ  በተመረኮዘ  ማንነት  ለመገንባት
                  ከተደረገው ጥረት ጋር የሚያያዝ ሲሆን፤ ሁለተኛው፤ ቀደም ሲል በአሃዳዊነት
                  ዘመን የደረሰውን በደል ለማከም በሚል በተወሰዱ መንግስታዊ እርምጃዎች
                  የተፈጠረው  ብሔረሰባዊ  አሃዳዊነት  (Ethnicised  unitarianism)  ናቸው።
                  የኢትዮጵያን ፖለቲካ ለማከም የሚደረገው ጥረት፣ የእነኚህን የማንነት ቀውሶች
                  ምንጭ ባግባቡ በመረዳት መፍትሄ መሻትን ይጠይቃል።
             iii.   የዘመናዊ ትምህርት በሃገሪቱ እየተስፋፋ መምጣት እና ከፊውዳላዊው ሥርዓት
                  ጋር ተያይዞ ከነበረው መጠነ ሰፊ ጭቆና ጋር መጣጣም አለመቻል ለተማሪው
                  እንቅስቃሴ  መጀመር  ዋነኛ  ምክንያት  ነበር።  ከዚህ  በተጨማሪ፣  ከላይ
                  በተጠቀሰው  አሃዳዊ  አገዛዝ  ምክንያት  ተፈጥሮ  የነበረው  የማንነት  ቀውስ
                  የተለያዩ  የማንነት  መብት  ጥያቄዎች  እንዲነሱ  አድርጓል።       በመሆኑም፣
                  በርካታው  ተማሪ  መሰረታዊ  የሆኑ  ሃገራዊ  እና  ሰብአዊ  የመብት  ጥያቄዎችን
                  እንደሃገራዊ  ዋነኛ  የለውጥ  መታገያ  ሲያነሳ፣  የተወሰኑት  ደግሞ  የብሄረሰቦች
                  የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት እንደዋነኛ መታገያ ሊያነሱ ችለዋል።
             iv.   ባለፉት  ስልሳ  አመታት  የማንነትን  ጥያቄ  በተመለከተ  የሚሰጡ  ትንታኔዎች
                  በአብዛኛው በፖለቲካው መስክ ከሚታየው የተቀነበበ ትንተና ድክመቶች የነጹ
                  ሊሆኑ አልቻሉም። ይህም፣ ባንድ በኩል በሃገሪቱ ምንም አይነት የብሔር ጭቆና
                  አልነበረም ከሚለው እና ገሃድ የነበረውን የማንነት በደሎች በሃገራዊ አንድነት
                  ለመሸፈን ከሚደረግ ሰጎናዊ አቋም አንስቶ ፍትሃዊ የሆነውን የብሔሮችን የራስን
                  በራስ የመወሰን መብት እስከ መገንጠል ድረስ በሚለጥጠው ተስፈንጣሪ የግራ
                  ዘመም አቋም ይገለጻል።
              v.   ከምህዳራዊ  አስተሳሰብ  አኳያ፣  የማንኛውም  ሰው  ማንነት  የበርካታ  ጥምር
                  መለያዎች መስተጋብር እንጂ በአንድ የተናጠል ባህርይ የሚገለጽ አይደለም።
                  ከዚህም የመጀመሪያው ማንነት፣ የተፈጥሮ ማንነት ሲሆን ይህም የሰው ልጅ
                  ከእንስሳቱ ዓለም የሚለየውን ሰብዓዊ ባህርይ የሚያጎናጽፈው ተፈጥሮዋዊው
   61   62   63   64   65   66   67   68   69   70   71