Page 71 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 71
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
የሁለቱም ዓለም የሴቶች እንቅስቃሴዎች፣ የሴቶችን የእኩልነት መብት በማረጋገጥ ረገድ
ባለፈው አንድ ምዕተ ዓመት ለታዩ አበይት ለውጦች የየራሳቸውን ድርሻ አበርክተዋል።
ሆኖም፣ አሜሪካንን ጨምሮ በበርካታ ምዕራባዊያን ሃገራት የሚገኙ ሴቶች
በፖለቲካም ሆነ በንግዱ አለም ተጭኖባቸው ያለውን ወንዴ-ሰራሽ የሥልጣን ገደብ (glass
ceiling) ሰብሮ ለመውጣት ያለባቸውን ፈተና ለተመለከተ፣ ሶሻሊስታዊ ቅኝት ያላቸው
ሃገሮች ሁሉን አቀፍ የሴቶች የእኩልነት መብት መከበርን በተመለከተ በተሻለ ደረጃ ላይ
እንደሚገኙ መረዳት ይቻላል። ለዚህም እንደማሳያ፣ በተለይ ስዊድንን በመሰሉ
ስካንዲኔቪያን ሃገሮች ያለውን ሰፊ የሴቶች መብት ጥበቃ እና የአመራር ተሳትፎ መጥቀስ
ይቻላል።
ወደሃገራችን ሁኔታ ስንመጣ፣ እህቶቻችን እና እናቶቻችን እንደየትኛውም
የዓለማችን ማህበረሰብ በተመሳሳይ የአባዊነት ሥርዓት ለሚፈጠሩ የመብት ንፍገቶች እና
ጥሰቶች የተጋለጡ ነበሩ፤ ዛሬም ናቸው። ከዚህም በላይ፣ ከተለያዩ አካባቢያዊ ልማዶች እና
እምነቶች ጋር ለተያያዙ ተጨማሪ አድሎዎች እና ጥቃቶች ሲጋለጡ ኖረዋል። ያም ሆኖ ግን፣
በሃገሪቱ የረጂም ዘመን ታሪክ ውስጥ እጅግ ከፍተኛ ድርሻ የነበራቸው ንግሥቶች፤ እንስት
የጦር አበጋዞች እና የማህበረሰብ መሪዎች እንደነበሩም ተመዝግቧል። ከዚህም ባሻገር፣
በሃገራችን ታሪክ ውስጥ ጉልህ ስፍራ ከሚሰጣቸው ነገሥታት እና የማህበረሰብ መሪዎች
በስተጀርባ ብርቱ ሴቶች እንደነበሩ የሚያመላክቱ መረጃዎችም አሉ። በዚህ ረገድ፣ በታሪክ
ቀደምት ከሚባሉት በርካታ ሃገሮች በተሻለ የሃገራችን ሴቶች በሃገሪቱ የፖለቲካ ህይወት
ውስጥ የራሳቸውን አሻራ እንዳሳረፉ መረዳት ተገቢ ይሆናል።
ከዚህ በተጨማሪም፣ በአንዳንድ ማህበረሰቦች ውስጥ አንዲት ሴት በትዳር
ህይወቷ የሚያጋጥሟትን ጥቃቶች፣ ሴቶች ተሰባስበው በጋራ ለመከላከል የሚያስችሏቸው
ሥርዓቶች እንዳሏቸው ይነገራል። የኦሮሞ ሴቶች የሲቄ ሥርዓት ለዚህ አንድ ምሳሌ ነው፡፡
ከዚህም አልፎ፣ ቀደም ካሉ ዘመናት ጀምሮ ለሴቶች መብት በግንባር ቀደምትነት በመቆም
በየዘመኑ ተንሰራፍተው የነበሩ ኢፍትሃዊ አሰራሮችን ማስቀየር የቻሉ ቀደምት የሴቶች
መብት አቀንቃኞች እንደነበሩ የሚነገሩ ተረኮችም አሉ። ለዚህም እንደማሳያ፣ በ1870ዎቹ
በጉራጌ ማህበረሰብ ውስጥ ተነስተው የነበሩትን የሴቶች መብት አቀንቃኝ ወይዘሮ ቃቄ
ወርድወትን መጥቀስ ይቻላል። ይህም የሚያሳየው፣ ባሁኑ ሰዓት ባንዳንድ ወገኖች
ከምዕራባዊያን ሃገሮች እንደተኮረጀ ተደርጎ የሚነገርለት የሴቶች የመብት እንቅስቃሴ
በሃገራችንም ቀደም ብሎ የተጀመረ እንደነበር ነው።
በምህዳራዊ አስተሳሰብ መሰረት፣ ሴታዊነት ለማንኛቸውም ተፈጥሮአዊ እና
ማህበራዊ ምህዳር ቀጣይነት ዋነኛው መሰረት ነው። ይህም በአበይትነት ለሴቶች
በተሰጣቸው የእናትነት ምግባር የሚገለጽ ከመሆኑም በላይ ሌሎችም መስረታዊ የሆኑ እና
ከወንዶች በበለጠ ለሴቶች የተሰጧቸው ባህርያት አሉ። ከነዚህም ውስጥ አንዱ፣ የሌላ ሰውን
ችግር እንደራስ ሆኖ ለመረዳት እና ለመካፈል (empathy) ያላቸው ዝግጁነት ከብዙ ወንዶች
63