Page 67 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 67

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     የዘረ  መልእ  ማንነቱ  ነው።  ሁለተኛው  ማንነት፣  ማህበራዊ  ማንነት  ሲሆን
                     የማንኛችንም ማህበራዊ ማንነት ከቤተሰብ በሚተላለፉ የቋንቋ፣ የሃይማኖት፣
                     የባህል፣ እና፣ የልማዳዊ ሁነት ውርሶች የሚወሰን ይሆናል። ሶስተኛው ማንነት፣
                     ፖለቲካዊ ማንነት ሲሆን ይህም ከሃገረ መንግስት ምስረታ ታሪክ ጋር የተያያዘ
                     የዜግነት ማንነት ነው።
               vi.   በማህበራዊ  ማንነት  ላይ  የተመረኮዙ  የፖለቲካ  እንቅስቃሴዎች  ውጤታማ
                     እንዲሆኑ  ከተፈለገ  ሰብዓዊ  ማንነትን  በሚያከብር  እና  ለዘመኑ  በሚመጥን
                     የዜግነት  አመለካክት  ሊቃኙ  ይገባቸዋል።  ይህ  ካልሆነ፣  በብዙዎቹ  አንጋፋ
                     የብሔር ድርጅቶች ውስጥ ባሁኑ ስዓት እንደሚታየው ጠባብ ወደሆነ የመንደር
                     እና የቤተሰብ መጠቀሚያነት መሸጋገራቸው እና የግጭት እና ውዝግብ ምንጭ
                     መሆናቸው የማይቀር ይሆናል።
               vii.   ‘አትዮጵያዊውን  በአካል  ከኢትዮጵያ  ታወጣው  እንደሆነ  እንጂ  ኢትዮጵያን
                     ከኢትዮጵያዊው  ውስጥ  ማውጣት  አይቻልም’  የሚል  አባባል  አለ።  ይህም፣
                     የሃገሪቱ ህዝቦች ካሏቸው ጥልቅ ማህበራዊ እና ታሪካዊ መሰረት ጋር የተያያዘ
                     መሆኑ  አያጠያይቅም።     ከዚሁ  ጥብቅ  ትስስር  ጋር  በተያያዘ፣  ከሃገር  ውጭ
                     የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በተለያየ ወቅት በሃገሪቱ በተከሰቱ አበይት የፖለቲካ
                     ሁነቶችም ንቁ ተሳታፊ እንደነበሩ ይታወቃል። ስለሆነም፣ የኢትዮጵያ ፖለቲካ
                     ሲነሳ፣ በውጭ ሃገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የነበራቸውን ጠቃሚም ሆነ ጎጂ
                     አስተዋጽኦዎች አለማንሳት አይቻልም።
              viii.   ከሺህ  ዘጠኝ  መቶ  ስልሳዎቹ  ወዲህ  ያለውን  የኢትዮጵያውያን  ዳያስፖራ
                     የፖለቲካ ተሳትፎ በምንመለከትበት ጊዜ በዋነኝነት ሶስት የዳያስፖራ ፖለቲካ
                     ዘመኖች እንዳሉ እናያለን። እነኚህም፣ በሃገሪቱ የቅርብ ዘመን የፖለቲካ ታሪክ
                     ውስጥ ታላላቅ የለውጥ አጋጣሚዎችን ከሚወክሉት የ1966፣ የ1983 እና የ2010
                     የለውጥ አጋጣሚዎች ጋር የተያያዙ ሆነው እናገኛቸዋለን። በእነዚህ የለውጥ
                     አጋጣሚዎች ዳያስፖራው ጠቃሚም ጎጂም አበርክቶት እንደነበረው ይነገራል።
               ix.   ዳያስፖራው  ሊያበረክት  የሚችለውን  በጎ  አስተዋጽኦ  ለማጠናከር፣
                     በእንቅስቃሴው ውስጥ የሚታዩ አንዳንድ መሰረተ ቢስ እምነቶችን (myths)
                     ማከም ይገባል። የመጀመሪያው፣ አንዳንድ የዳያስፖራ የፖለቲካ ዘመን መሪዎች
                     እና  አቀኝቃኞች  ለተፈጠረው  የለውጥ  ሂደት  ያበረከቱትን  አስተዋጽኦ  እጅግ
                     አግዝፈው ማየታቸው ነው። ከዚህም የተነሳ፣ ለውጡ ያለ እነሱ አመራር የትም
                     ሊደርስ አይችልም ብለው እስከማመን ይደርሳሉ።
                x.   በማንኛውም ምህዳር ውስጥ ሊመጣ የሚችል ለውጥ ዋነኛው መሰረቱ በዚያው
                     ምህዳር ውስጥ ያለው ውስጣዊ መስተጋብር (internal dynamics) ሲሆን
                     የውጫዊ ሁኔታዎች ድርሻ የዚህን የለውጥ ፍጥነት ከማሳለጥ ወይም ከማዘግየት
                     ያለፈ አይሆንም።



                                                                        59
   62   63   64   65   66   67   68   69   70   71   72