Page 68 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 68

ደስታ መብራቱ


             xi.   ሁለተኛው፣ ለሃገሪቱ ለውጥ ታላቅ ድጋፍ እና አበርክቶት ሊያረግ የሚችለው
                  ዝምተኛው  ብዙሃን  ዳያስፖራ  በጋራም  ሆነ  በተናጠል  እራሱ  ሊኖረው
                  የሚችለውን ሚና አሳንሶ ማየቱ ነው። በዚህም የተነሳ፣ የበርካታው ዳያስፖራ
                  ኢትዮጵያዊ  በጎ  ፈቃድ  የጥቂት  ብልጣብልጥ  ፖለቲከኞች  እና  የማህበራዊ
                  ሚድያው አርበኞች መጠቀሚያ ሲሆን ይታያል።
             xii.   ስለሆነም፣ የዚህች ሃገር የነገ እጣ ፋንታ የሚያስጨንቀን ወገኖች ዝምታችንን
                  ሰብረን ባለን እውቀት እና አቅም እየተካሄደ ያለው ለውጥ ሁሉንም አካታች
                  ወደሆነ እና የዜጎችን ሁለንተናዊ የዲሞክራሲ እና የልማት ፍላጎቶችን ሊያሟላ
                  ወደሚችል ሥርዓት እንዲሸጋገር ማገዝ ይኖርብናል።
   63   64   65   66   67   68   69   70   71   72   73