Page 73 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 73

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                                                       26
             የሴታዊነት  መሰረታቸውን  የጠበቁ  ጠንካራ  ሴት  አመራሮች   እያየን  በመሆኑ  የእነርሱን
             አርአያነት  ማበራከት  ያስፈልጋል።  ባጭር  አነጋገር፣  በአሁኑ  ወቅት  ከሴቶቻችን  በእጅጉ
             የሚያስፈልገን በሴታዊነት የተቃኘ አመራራቸው እንጂ ወንዳዊነትን የተላበሰ መሪነታቸው
             አይደለም።

                     ከላይ  የተዘረዘሩትን  አካሄዶች  በዘላቂነት  ተግባራዊ  ለማድረግ  ሴታዊነትን
             ከመሰረቱ  ሊያጠናክሩ  የሚያስችሉ  ተቋማዊ  እርምጃዎችን  መውሰድ  ያስፈልጋል።  ከዚህ
             ውስጥ የመጀመሪያው፣ በቤተሰብ ደረጃ ሴታዊነት ያለውን በርካታ ማህበራዊ ጠቀሜታ
             በተመለከተ ያለውን ግንዛቤ ማሳደግ እና ከዚህ በተቃራኒው ያሉ ልማዳዊ አስተሳሰቦችን
             ማስወገድ  ነው።  ከዚህ  በተጨማሪ፣  የትምህርት  ሥርዓት  አደረጃጀትም  ሆነ  አሰጣጥ
             ለሴታዊነት አመለካከት መጠናከር በሚያስችል መልኩ እና በሁለቱ ጾታዎች            ማህበራዊ
             ባህሪያት መካከል ያሉትን በርካታ ተደጋጋፊነት እና ተመጋጋቢነት በሚያጠናክር መልኩ
             መቃኘት ይኖርበታል።ለእነኚህ ተቋማዊ እርምጃዎች ትኩረት እንዲሰጥ በማድረግ ረገድ፣
             በሴቶች ሁለንተናዊ የመብት ጥበቃ ላይ የሚሰሩ ሃገር በቀል ድርጅቶች ግንባር ቀደም ድርሻ
             ይኖራቸዋል።    በአጠቃላይ፣  ሁለንተናዊ  የሴታዊነት  ድርሻን  ማጠናከር ለረጂም  ዘመናት
             በውጥረት የታጀበውን ፖለቲካችንን ወደ ተረጋጋ እና የሰከነ ፖለቲካ ለማሸጋገር ከማገዙም
             በላይ አካታች እና ዘላቂ ልማትን በማረጋገጡም በኩል የራሱ ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል።


















             26  ለዚህም እንደምሳሌ፣ ለበርካታ ዓመታት በቅርበት እማውቃቸውን ፕሬዚዳንት ሣህለወርቅ
             ዘውዴን እና ከ2010 ለውጥ በኋላ ሥራቸውን በመከታተል ያወኳቸውን ወይዘሮ ሙፈሪያት
             ካሚልን መጥቀስ ይቻላል።
                                                                        65
   68   69   70   71   72   73   74   75   76   77   78