Page 78 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 78
ደስታ መብራቱ
የክፍል አምስት ቁልፍ ሐሳቦች
i. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከተወደሱበት
አበይት እርምጃዎች አንዱ በርካታ ሴት አመራሮችን በመንግስታቸው ውስጥ
ማካተታቸው እና በዘመናዊው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ታሪክ ውስጥ የመጀመርያ
የሆኑትን የሃገሪቱ ሴት ርዕሰ ብሔር እንዲሾሙ ማድረጋቸው ነው። ይህ እና
በሌሎችም የፖለቲካ ድርጅቶች ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ የህዝብ ተቋማት
የተጀመሩ ቀና እርምጃዎች ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ ከተፈለገ ሴታዊነት
(Feminism) ባንድ ምህዳር ውስጥ ያለውን ምሉዕ ድርሻ በመረዳት ላይ
የተመረኮዙ ሊሆኑ ይገባቸዋል።
ii. ዘመናዊውን የተደራጀ የሴቶች የመብት እንቅስቃሴ አነሳስን ስንመለከት በ 19ኛው
ክፍለ ዘመን የነበሩት አሜሪካዊቷ የሴኔካ ፏፏቴ መግለጫ አዘጋጅ ወይዘሮ
ኤልሳቤጥ ስታንተን እና ጀርመናዊቷ ሶሻሊስታዊ የሴቶች መብት አቀንቃኝ
ወይዘሮ ክላራ ዜትኪን በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳሉ።
iii. በሃገራችንም፣ በተመሳሳይ ወቅት በጉራጌ ማህበረሰብ ውስጥ ተነስተው
የነበሩትን የሴቶች መብት አቀንቃኝ ወይዘሮ ቃቄ ወርድወትን መጥቀስ ይቻላል።
ይህም የሚያሳየው፣ ባሁኑ ሰዓት ባንዳንድ ወገኖች ከምዕራባዊያን ሃገሮች
እንደተኮረጀ ተደርጎ የሚነገርለት የሴቶች የመብት እንቅስቃሴ በሃገራችንም
ቀደም ብሎ የተጀመረ እንደነበር ነው።
iv. በምህዳራዊ አስተሳሰብ መሰረት፣ ሴታዊነት ለማንኛቸውም ተፈጥሮአዊ እና
ማህበራዊ ምህዳር ቀጣይነት ዋነኛው መሰረት ነው። ይህም በአበይትነት
ለሴቶች በተሰጣቸው የእናትነት ምግባር የሚገለጽ ሲሆን ሌሎችም መስረታዊ
የሆኑ እና ከወንዶች በበለጠ ለሴቶች የተሰጧቸው ባህርያት አሉ።
v. ከነዚህም ውስጥ አንዱ፣ የሌላ ሰውን ችግር እንደራስ ሆኖ ለመረዳት እና
ለመካፈል (empathy) ያላቸው ዝግጁነት ከብዙ ወንዶች የበለጠ መሆኑ ነው።
ሌላው፣ ኑሮን ለማሸነፍ በሚደረገው ትግል ውስጥ ካላቸው ቁልፍ ድርሻ ጋር
በተያያዘ ፈታኝ ሁኔታዎችን ለመሻገር ያላቸው የስሜት (survival instinct)
ዝግጁነት ነው።
vi. ከዚህ በተጨማሪ፣ ተፈጥሮአዊው ዑደትን ለማስቀጠል ካላቸው ልዩ ኃላፊነት
እና ድርሻ ጋር በተያያዘ ከተፈጥሮአዊው ምህዳር ጋር ያላቸው ቅርበት እና
ተዛማጅነት (ecological sensibility) ነው። ከሁሉም በላይ በሰፊው ካለብን
የፖለቲካ ህመም ለመፈወስ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ሊኖረው የሚችለው ባህሪ፣
ኃይልን መሰረት ካደረገ (hard power) አመራር እና የግጭት አፈታት ይልቅ
ስሜትን በማለስለስ እና በማሳመን (soft power) ላይ ለተመረኮዘ መፍትሄ
ያላቸው ብልህነት ነው።
vii. እነኚህ እና እነኚህን የመሳሰሉ በርካታ የሴታዊነት ባህርያትን በውጤታማነት
ለመጠቀም የአመራር ቦታ የሚይዙ እህቶቻችን ወንዳዊ ሃይለኝነትን
(machismo) እንዲላበሱ የሚያስገድዱ ሁኔታዎችን መከላከል እና በሴታዊነት