Page 79 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 79

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     ልዩ  ባህሪያቸው  ላይ  በመመርኮዝ  ሊያበረክቱ  የሚችሉት  አስተዋጽኦ  ላይ
                     ማተኮር ይኖርባቸዋል። ይህ ፈተና፣ በወንዳዊ አስተሳሰብ  ከተቃኘው ተቋማዊ
                     ባህላችን አኳያ ሲታይ በእጅጉ ፈታኝ ሊመስል ይችላል። ነገር ግን፣ እንደምሳሌ
                     ሊወሰዱ የሚችሉ የሴታዊነት መሰረታቸውን የጠበቁ ሴት አመራሮች እያየን
                     በመሆኑ የእነርሱን አርአያነት ማበራከት ያስፈልጋል።
              viii.   ባለፉት  ጥቂት  ዓመታት  ውስጥ  የሴቶችን  የአመራር  እና  የፖለቲካ  ተሳትፎ
                     የሚያበረታቱ እርምጃዎች በመወሰድ ላይ ይገኛሉ። ይህ እንዳለ ሆኖ፣ ለረጂም
                     ዘመናት በሁሉም ተቋማዊ አደረጃጀቶች እና በአብዛኛው ህብረተሰብ ውስጥ
                     ተንሰራፍቶ የኖረው የወንዳዊነት አመለካከት ለብዙዎቹ ሴት አመራሮች ታላቅ
                     ፈተና እንደሚሆኑባቸው ይገመታል።
               ix.   ከቅርብ  ጊዜ  ወዲህ፣  አንዳንድ  የፖለቲካ  ተንታኞች  እና  አቀንቃኞች  በሴት
                     አመራሮች  ላይ  ግልጽ  ዘመቻ  የጀመሩ  ይመስላል።  ማንኛውም  የመንግስት
                     አመራር  ለሚሰራው  ስራ  ተጠያቂነት  ያለበት  መሆኑ  ባይካድም፣  በተዛባ
                     አመለካከት  ላይ  ተመርኩዞ  በሴት  አመራሮቻችን  ላይ  ብያኔ  ማሳለፍ
                     የተጀመረውን መልካም ጥረት ስለሚያዳክም ሊታረም ይገባዋል።
                x.   በፌዴራል  መንግሥቱ  እና  በትግራይ  ክልል  መንግሥት  መካካል  የነበረው
                     ውጥረት ከፍተኛ ደረጃ በደረሰበት ወቅት የሠላም ሚኒስትር የሆኑት ወይዘሮ
                     ሙፈሪያት ካሚል በድፍረት ወጥተው የተናገሩት ሃሳብ በማህበራዊ ሚዲያው
                     ዘርፍ ውዝግብ አስነስቶ ከርሞ ነበር።
               xi.   ይህ፣ ከውጥረት ይልቅ ስክነትን፣ ከወታደራዊ ፍጥጫ ይልቅ በጠረጴዛ ዙሪያ
                     ቀርቦ መነጋገርን የሚያሳስብ ንግግር የ ’ቁረጠው ፍለጠው ሃይ ዘራፍ ፖለቲካ’
                     አራማጆቾን ያስቆጣበት ዋነኛው ምክንያት ቀደም ሲል የቀረበውን የሴታዊነት
                     ልዩ ባህርያት እና ጠቀሜታ ባለመረዳታቸው መሆኑ ግልጽ ነው።
               xii.   ወ/ሮ ሙፈሪያት ተናገሩት የተባሉት ነጥቦች ለሌሎች መሰል የሃገራችን የፖለቲካ
                     ችግሮች  መፈታት  አይነተኛ  አስተዋጽኦ  ሊያደርጉ  የሚችሉ  በመሆናቸው
                     ወደፊትም  ይበልጥ  ሊበረታቱ  እና  ሊደገፉ  ይገባል።  ይህ  ንግግራቸው፣
                     በወንዳዊነት መንፈስ የተጫነብንን ‘የሃይ ዘራፍ’ ፖለቲካ ለማከም የሴታዊነት
                     አመለካከት  ሊኖረው  የሚችለውን  ጉልህ  አስተዋጽኦ  በተጨባጭ  የሚያሳይ
                     በመሆኑ  የኢትዮጵያ  ፖለቲካ  ብዙ  ሙፈሪያቶች  እንደሚያስፈልገው  አበክረን
                     መግለጽ እንፈልጋለን።
               xiii.   በመሆኑም፣ በማናቸውም ወቅት ብሔራዊ መግባባትን ለማጠናከር በየደረጃው
                     የሚካሄዱ ውይይቶች የሴታዊነት ልዩ ባህርያት ሊያበረክቱ የሚችሉትን ጠቃሚ
                     አስተዋጽ  ግምት  ውስጥ  ማስገባት  እና  በተገቢው  መንገድ  መጠቀም
                     ይኖርባቸዋል።    ታላቁ  የሳይንስ  ምሁር  አልበርት  አይንሽታይን  እንዳሉት
                     ‘የዛሬውን ችግራችንን በትናንትናው መንገድ ለመፍታት መሞከር ከንቱ ድካም
                     ነው’።



                                                                        71
   74   75   76   77   78   79   80   81   82   83   84