Page 84 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 84

ደስታ መብራቱ


                  ባሁኑ ሰዓት በስራ ላይ ያለው የፌዴራሉ ህገ መንግስት ለማንኛውም ጤናማ
           ህገ መንግስታዊ ሥርዓት አስፈላጊ የሆኑ የዜጎችንና የማህበረሰቦችን መብቶች የሚያስከብሩ
           በርካታ  መሰረታዊ  የህግ  አንቀጾችን  የያዘ  መሆኑ  ይታወቃል።  ነገር  ግን፣  ከዚህ  በላይ
           ከተጠቀሰው  መደበላለቅ  ጋር  በተያያዘ  ህገ  መንግስቱን  የአብዮታዊ  ዲሞክራሲ  ቅኝት
           የሚሰጡ አንዳንድ አንቀጾችም አሉት። ይህ ይዘትም ህገ መንግስቱን ባንዳንድ ሁኔታዎች
           እርስ  በርሱ  የሚጣረስ  አድርጎታል።  እንዲህ  አይነቱ  የግጭት  ይዘት  በተለይም  የህገ
           መንግሥታዊው  ሥርዓት  ዋነኛ  አካል  የሆኑት  የክልል  መስተዳድሮች  ባጸደቋቸው  ህገ
           መንግስቶች ውስጥ እጅግ ገንነው ይታያሉ።
                   ከዚህ  በተጨማሪም፣  ህገ  መንግሥቱን  ለማስፈጸም  የተቋቋሙ  ተቋማትንም
           የአብዮታዊ ዲሞክራሲ ቅኝት እንዲይዙ በመደረጉ በህገ መንግሥቱ ውስጥ ያሉ በርካታ
           ጠቃሚ  ሃሳቦች  እንዲኮላሹ  አድርጓቸዋል።  ይህንን  ችግር  ለማስወገድ፣  በፌዴራል  ህገ
           መንግስቱ  ውስጥ  ያሉ  የተቃርኖ  ምንጮችን  መለየትና  የክልሎች  ህገ  መንግስቶችን
           ከፌዴራሉ ህገ መንግስት ጋር የማጣጣም ስራ መስራት ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ተግባር
           ነው። በተለይም በፌዴራሉ ህገ መንግስት የተከበረውንና ኢትዮጵያ ዓለም አቀፋዊ ግዴታ
           የገባችባቸውን የዜጎችን በየትኛውም የሃገሪቱ ክፍል በህይወት የመኖር፣ የመስራት፣ ሃብት
           የማፍራት፣ የመምረጥና የመመረጥ መብቶቻቸውን ማረጋገጥ ከሁሉም ቀዳሚው ተግባር
           መሆን  ይኖርበታል።  እነኝህ  መሰረታዊ  መብቶች  በሚጣሱበት  ወቅትም  የማንኛውንም
           ክልል ግብዣም ሆነ ፈቃድ ሳይጠብቅ ህገ መግስቱን ማስከበር የፌዴራሉ መንግስት ግዴታ
           ሊሆን ይገባል። እነኚህን መሰረታዊ መብቶች ማስከበር በምንም አይነት ሁኔታ በፌዴራል
           ህገ  መንግስቱ  የተረጋገጡ  የቡድን  መብቶችን  ሊሸራርፍ  ወይንም  የሚሸራርፍ  ተደርጎ
           ሊወሰድም አይገባውም።
                  ሌላው ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን አደጋ ላይ የጣለው ተቋማዊ ችግር፣ በህግ
           አውጭው፣ በህግ ተርጓሚውና በህግ አስፈጻሚው መካከል ያለው ቅጥ የለሽ መደበላለቅ
           ነው።  ይህ  ሁኔታ፣  በእነኚህ  ሶስት  ቁልፍ  ህገ  መንግስታዊ  ተቋሞች  መካከል  ሊኖር
           የሚገባውን  የትብብርና  የቁጥጥር  ሥርዓቶች  ከማመንመኑም  በላይ  በህገ  መንግስቱ
           የተከበሩ ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ክፉኛ እንዲሸረሸሩ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ
           አድርጓል። ባለፉት ጥቂት የሽግግር ዓመታት ውስጥ፣ በተለይ የህግ ተርጓሚውን ነጻነት
           ለማረጋገጥ በፌዴራል ደረጃ የተወሰዱ አንዳንድ እርምጃዎች መኖራቸው ይታወቃል። ነገር
           ግን፣ አጠቃላይ የሽግግር ሂደቱን ቀደም ሲል ከነበረው ከፍተኛ መዋቅራዊ መደበላለቅ
           ለማላቀቅ  እጅግ  በርካታ  ስራዎች  እንደሚቀሩ  የሚያመላክቱ  በርካታ  ሁነቶች  ዛሬም
           ይታያሉ።

                  በዚህ፣  መዋቅራዊ  መደበላለቅን  መስመር  ለማስያዝ  በሚወሰደው  እርምጃ
           ውስጥ  ሊካተት  የሚገባው  ሌላው  አቢይ  ጉዳይ  የህዝብ  አስተዳደር  (civil  service)
           መዋቅሩን ከፖለቲካዊ መዋቅሩ የመለየት ጉዳይ ነው። ምንም እንኳን በምርጫ አሸናፊ
           የሆነ  የፖለቲካ  ድርጅት  አሸናፊ  ያደረጉትን  ፖሊሲዎቹን  የሚያስፈጽሙለትን  መሪዎች
           በበላይ  ሃላፊነት  መመደቡ  ተገቢ  ቢሆንም፣  አጠቃላይ  የህዝብ  አስተዳደር  መዋቅሩን
   79   80   81   82   83   84   85   86   87   88   89