Page 86 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 86

ደስታ መብራቱ


                  የዛሬ መሪዎቻቸን ከዚህ ቀደም በእንዲህ አይነት ሁኔታ ተፈጥረው የነበሩ መሰል
           መልካም አጋጣሚዎችን ባለመጠቀማችን ከገባንበት ቀውስ ተምረዋል ወይም ይማራሉ
           የሚል እምነት አለን። ይህ ወቅት፣ የሁሉም ፖለቲካ መሪዎች አስተዋይነትና አርቆ አሳቢነት
           የሚለካበት ወቅት እንደመሆኑ፤ ሃገራዊ አንድነቱ የፈጠረውን መልካም አጋጣሚ ለህዝቦች
           ዘላቂ ሰላም፣ እድገትና ልማት ማረጋገጥ በሚያስችል መልኩ አለመጠቀም ከፍተኛ የታሪክ
           ተወቃሽነት  የሚያስከትል  ይሆናል።  ከእንዲህ  ዓይነቱ  ተወቃሽነት  ለመዳን፣  በአንድ
           የፖለቲካ ርዕዮተ ዓለም ከታጠረ የተዐብዮ ተረክ በመውጣት ዓይነታዊ የለውጥ ተረኮችን
           በትብብራዊ አስተሳሰብ ለማበልጸግ ዝግጁ መሆንን ይጠይቃል።
   81   82   83   84   85   86   87   88   89   90   91