Page 85 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 85

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             ፖለቲካዊ  ቅኝት  መስጠት  ተጠያቂነትን  የሚቀንስ  ከመሆኑም  በላይ  የአገልግሎት
             ውጤታማነትንና መልካም አስተዳደርን የሚያዳክም ይሆናል። ከሁሉም በላይ፣ እንዲህ
             አይነቱ መደበላለቅ በቅርቡ በሰሜናዊው የሃገራችን ክፍል ጎልቶ እንደወጣው፣ አጠቃላይ
             መንግስታዊ  ተቋማትን  የጥቂት  አምባገነን  ቡድኖች  እስረኛና  መጠቀሚያ  (captive)
             እንዲሆን ያደርገዋል። በዚህ ረገድ፣ በስልጣን ላይ ያለው ፓርቲም ሆነ ተፎካካሪ ፓርቲዎች
             መንግስታዊ  ያስተዳደር  ተቋማትን  ከዚህ  አይነቱ  ፈተና  ነጻ  እንዲሆኑ  ጥረት  ማድረግ
             ይኖርባቸዋል።

                     በቅርቡ  በሃገራችን  ከተከሰተው  አስቸጋሪ  ሁኔታ  ጋር  በጥብቅ  የሚተሳሰረው
             ሌላው መዋቅራዊ ችግር ለዘመናት ሰፍኖ የኖረው የሀገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት በየወቅቱ
             ላሉ የአገዛዝ ሥርዓቶች ጠባቂና አገልጋይ የማድረግ ዝንባሌ ነው። አሁን በስራ ላይ ያለው
             የፌዴራል ህገ መንግስት፣ የመከላከያ ሰራዊቱ ከማናቸውም ፖለቲካዊ ወገናዊነት ነጻ ሆኖ
             የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና ህገ መንግስታዊ ሥርዓቱን ከጥቃት ይጠብቃል ይላል። ይህ ድንጋጌ
             በአንድ  ሃገር  ውስጥ  የተረጋጋ  ህገ  መንግስታዊ  ሥርዓት  እንዲኖር  ከሚያደርጉ  ቁልፍ
             ድንጋጌዎች መካከል ዋነኛው ነው። ያም ሆኖ፣ ለሃያ ሰባት ዓመታት በሀገሪቱ ሰፍኖ የቆየው
             የአብዮታዊ  ዲሞክራሲ  ቅኝት  ወደ  ሰራዊቱ  ዘልቆ  በመግባት  አብዛኛውን  የሰራዊቱን
             አደረጃጀትና አመራር ፖለቲካዊ ይዘት እንዲኖረው አድርጎት ቆይቷል።

                     ባለፉት  ሁለት  የሽግግር  ዓመታት፣  ይህንን  ሁኔታ  ለመቀየርና  ሰራዊቱን
             ከማናቸውም ፖለቲካዊ አደረጃጀት ነጻ ለማድረግ በርካታ የአስተሳሰብ (indoctrination)
             እና  መዋቅራዊ  ለውጥ  ስራ  እንደተሰራ  ተነግሯል።  ነገር  ግን፣  በቅርቡ  በሰሜን  እዝና
             በመከላከያ ሰራዊት መዋቅር ውስጥ የተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት በዚህ ረገድ ገና ብዙ ቀሪ
             ስራ እንደሚኖር አመላክቷል። ስለሆነም፣ መንግስትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው የፖለቲካ
             ቡድኖች ይህንን ለማስተካከል ጥቅል ከሆነ ነቀፌታ እና ምልከታ በጸዳ መልኩ ሁኔታውን
             ለማጥራት ከፍተኛ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪም፣ የሃገር ህልውናን
             እስከ  መፈታተን  የደረሰውን  የክልሎች  የልዩ  ኃይል  አደረጃጀት  ወደ  ህገ  መንግስታዊ
             የአደረጃጀት ሥርዓት ማስገባት ሌላው አቢይ ተግባር ነው።

                     በመጨረሻም፣ ከዚህ ቀደም በተፈጠሩ  ሃገራዊ ጥቃቶች  ወቅት  እንደታየው፣
             በሰሜኑ እዝ የመከላከያ ሰራዊት ላይ የተፈጸመው ጥቃት ከፍተኛ የሆነ ሀገራዊ የአንድነት
             ስሜት ፈጥሯል። ይህ ከሚያጎናጽፈው መልካም አጋጣሚዎች አንዱ ሃገራዊ መግባባትን
             ለማጠናከር የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መፍጠሩ ነው። ይህንን መልካም አጋጣሚ በቅጡ
             በመረዳት  የብልፅግና  ፓርቲም  ሆነ  ተፎካካሪ  ፓርቲዎች  ሃገሪቱን  ወደፊት  ሊያሻግሩ
             በሚያስችሉ  አበይት  ሃገራዊ  ጉዳዮች  ላይ  በመወያየት  ቀጣዩን  ምርጫ  ነፃና  ተዓማኒ
             ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል።





                                                                        77
   80   81   82   83   84   85   86   87   88   89   90