Page 81 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 81

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


                     ከዚህ  በተቃራኒው፣  ተቋማዊ  ተረኮች  አንድን  የተወሰነ  የማህበረሰብ  ክፍል
             ወይም  ቡድን  ኢኮኖሚያዊ፣  ፖለቲካዊ  እና  ማህበራዊ  ዓላማዎች  በሚጠቅም  መልኩ
             የሚቀረጹ ናቸው። ተቋማዊ ተረኮች፣ ከአካታችነት (power with) ይልቅ ገዢነት (power
             over)፣ ከመደጋገፍ ይልቅ መቃቃር፣ ከጋራ እድገት ይልቅ ራስ ወድነት (egoism) ጎልቶ
                             30
             የሚታይባቸው  ናቸው ።እንዲህ  ዐይነት  ተረኮች  በህብረተሰቡ  ውስጥ  የሚኖራቸውን
             ተቀባይነት ለማጠናከር ሲሉ፣ ሰፋ ያለ ተቀባይነት ያለውን ማህበረሰባዊ ተረክ በመጥለፍ
             ለራሳቸው  ውሱን  ዓላማ  በሚጠቅም  መልኩ  ሲያራምዱት  ይስተዋላል።    ይህንን
             ለማሳካትም፣ በነባር ማህበረሰባዊ ተረኮች ውስጥ ስሜታዊ ምላሽ የሚያጭሩ ጉዳዮችን
             (emotive issues) በማግነን ይታወቃሉ።  በመሆኑም፣ ለአብዛኞቹ በዓለማችንም ሆነ
             በሀገራችን  ለተከሰቱት  ጦርነቶች  እና  የእርስ  በእርስ  ግጭቶች  ዋነኛ  መነሻዎች  ናቸው።
             የተቋማዊ  ተረኮች  ልዩ  ባህርያት፣  በአብዛኛው  ለራስ  አገልጋይ  (self-serving)  በሆኑ
             ተጠቃሚዎች ከተጠለፈው ማህበራዊ ሚዲያ ጋር ባለው ተጣጣሚነት የተነሳ ባሁኑ ወቅት
             የብዙ ሃገሮች ፈተና በመሆን ላይ ይገኛል። ይህንን ፈተና ለመሻገር አይነተኛው መፍትሔ፣
             ዓይነታዊ የለውጥ ተረኮችን ለማበልጸግ ጥረት ማድረግ ይሆናል።

                                                          31
             6.1 ችግሩን ከስሩ ለመንቀል፣ መዋቅራዊ ምንጩን ማድረቅ

                     በምህዳራዊ  አስተሳሰብ  መሰረት፣  በልዩ  ልዩ  መልኩ  የሚከሰቱ  የተፈጥሮ
             አደጋዎች  በተፈጥሮአዊው  ምህዳር  ውስጥ  ያሉ  ከመጠን  ያለፉ  ከባቢያዊ  መዛባቶችን
             ለማስተካከል የሚከሰቱ ተፈጥሮአዊ ሁነቶች ናቸው። ዛሬ በዓለም ዙሪያ በተጠናከረ ሁኔታ
             እየተከሰተ ያለው ድርቅ፣ ጎርፍ፣ አውሎ ነፋስ (tornedo)፤ ሰደድ እሳት እና የባህር ማእበል
             (hurricane)  ሁሉ ተፈጥሮአዊው ምህዳር የሚደርስበትን ከባቢያዊ መዛባት ለማስተካከል
             የሚጠቀምባቸውን  ሂደቶች  የሚያመላክቱ  ናቸው።         በተመሳሳይ  መልኩ፣  ግጭቶችና
             ጦርነቶች  ባንድ  ማህበረሰብ  ውስጥ  ወይም  በሀገሮች  መካከል  ያሉ  እና  ጥልቅ  የሆኑ
             ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ቅራኔዎች መገለጫ ናቸው። በዕውቀትና አስተውሎት
             ላይ  በተመረኮዙ  አስተሳሰቦችና  አካሄዶች  በመጠቀም  ባንድ  ሁኔታ  ውስጥ  የተፈጠሩ
             መዛባቶችንና  ግጭቶችን  መፍታትና፣  ሚዛናዊ  የሆነ  አካሄድን  በመከተል  አብዛኛዎቹን
             ከባቢያዊም ሆነ ፖለቲካዊ ቀውሶች ወደ ከፋ ጉዳት እንዳያመሩ ማድረግ ይቻላል።
                     ወደ ሃገራችን ሁኔታ ስንመጣ፣ ለእንዲህ አይነቱ ጤናማ አካሄድ ያለው ዝግጁነት
             ደካማ በመሆኑ ብዙዎቹ ልዩነቶች በኃይል እና በግጭት ሲቋጩ ኖረዋል። በቅርቡም፣
             ከትግራይ ክልል መሪዎች በኩል  ለሰላማዊ  መፍትሔ  የነበረው ዝግጁነት ይበልጥ  አናሳ
             በመሆኑ የብዙዎቹን ህይወት ላጠፋ እና የሚሊዮኖችን ኑሮ ላመሰቃቀለ አሳዛኝ ጦርነት
             ተዳርገናል።  አንዳንድ  ፖለቲከኞችና  ተንታኞች  ይህ  ጦርነት  ህወሓትን  በመደምሰስ


             30  እንዲህ ዓይነት ተቋማዊ ተረኮች ብዙውን ጊዜ ህዝበኝነት (populism) ለተጠናወታቸው
             የፖለቲካ መሪዎች እና ቡድኖች ዋነኛ መጠቀሚያ ናቸው።
             31  የዚህ ክፍል አብዛኛው፣ ህዳር 11 2013 በወጣው አዲስ አድማስ ጋዜጣ ታትሟል።
                                                                        73
   76   77   78   79   80   81   82   83   84   85   86