Page 77 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 77

ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ


             ሊያወግዙት  እና  በጽኑ  ሊታገሉት  ይገባል።  በተለይም፣  በአብዛኛው  ማህበረሰብ  እንደ
             አቅጣጫ አመላካች (opinion makers) ተደርገው የሚገመቱ ወገኖች ከእንዲህ አይነቱ
             ስህተት ሊጠበቁ ይገባል። ይህም ሲባል፣ ማንኛውም ባለሥልጣን ለሚፈጽማቸው ጥፋቶች
             ሙሉ ኃላፊነት እና ተጠያቂነት ሊኖረው እንደሚገባ በማመን ነው።

                     በአምስተኛ  ደረጃ  የተነሳው፣  እንዴት  የፌዴራሉን  እና  የክልሉን  መንግስት
             በእኩልነት በማስቀመጥ ሁለቱንም ወገኖች ‘ሰከን በሉ’ ብለው ይናገራሉ የሚል ነበር።
             በመጀመሪያ  ደረጃ፣  እኔ  እንደተረዳሁት  ወ/ሮ  ሙፈሪያት  ሰከን  በሉ  ያሉት  በሁለቱም
             ወገኖች ያሉ አንዳንድ ፖለቲከኞችን እንጂ መንግስታቱን አይደለም። በርግጥም፣ በሁለቱም
             ወገኖች  ያሉ  አንዳንድ  የፖለቲካ  መሪዎች  በተለያየ  ወቅት  እየወጡ  የተናገሩት  ነገር
             ውጥረቱን ይበልጥ የሚያከሩ እንጂ ወደ መፍትሔ ለመሄድ የሚያግዙ አልነበሩም። ይህም፣
             በስተመጨረሻ ለምን ዓይነት ጥፋት እና ውድመት እንደዳረገን ታይቷል። ከሌሎች ሃገሮች
             ተመክሮ  እንደታየው፣  ለሰላማዊ  መፍትሄ  የሚደረግ  ማንኛውም  ጥረት  የመጀመሪያው
             እርምጃ ሁሉም ወገኖች ውጥረትን ከሚያባብሱ አባባሎች (rhetoric) መታቀብ ይሆናል።
             በወቅቱ፣ በፌዴራል መንግስቱ እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል የነበረውን መካረር
             ለማርገብ እና ለመፍታት ከሁሉም ወገኖች በተለይም ከፌዴራል መንግስቱ ከምንም ጊዜ
             በላይ  ከፍተኛ  ሆደ  ሰፊነት  (magnanimity)  እና  ታጋሽነት  የሚጠበቅበት  ወቅት  ነበር።
             ይህንን ማድረግ ለሃገር እና ለህዝብ ታላቅ አክብሮት በማሳየት መከበርን የሚያስገኝ እንጂ
             በደካማነት የሚያስፈርጅ አልነበረም።

                     በአጠቃላይ፣  ወ/ሮ  ሙፈሪያት  ተናገሩት  የተባሉት  ነጥቦች  ለሌሎች  መሰል
             የሃገራችን የፖለቲካ ችግሮች መፈታት አይነተኛ አስተዋጽኦ ሊያድርጉ የሚችሉ በመሆናቸው
             ወደፊትም ይበልጥ ሊበረታቱ እና ሊደገፉ ይገባል። ይህ ንግግራቸው፣ በወንዳዊነት መንፈስ
             የተጫነብንን ‘የሃይ ዘራፍ’ ፖለቲካ ለማከም የሴታዊነት አመለካከት ሊኖረው የሚችለውን
             ጉልህ  አስተዋጽኦ  በተጨባጭ  የሚያሳይ  በመሆኑ  በድጋሚ  የኢትዮጵያ  ፖለቲካ  ብዙ
             ሙፈሪያቶች  ያስፈልገዋል  እንላለን።  በዚሁ  አጋጣሚ፣  በማናቸውም  ወቅት  ብሔራዊ
             መግባባትን  ለማጠናከር  በየደረጃው  የሚካሄዱ  ውይይቶች  የሴታዊነት  ልዩ  ባህርያት
             ሊያበረክት የሚችለውን ጠቃሚ አስተዋጽ ግምት ውስጥ ማስገባት እና በተገቢው መንገድ
             መጠቀም ይኖርባቸዋል።  ታላቁ የሳይንስ ምሁር አልበርት አይንሽታይን እንዳሉት ‘የዛሬውን
             ችግራችንን  በትናንትናው  መንገድ  ለመፍታት  መሞከር  ከንቱ  ድካም  ነው’።  ስለዚህም፣
             ፖለቲካችንን ‘ከወንዳዊነት’ ባህሪው ቀስ በቀስ በማላቀቅ ጊዜው በሚጠይቀው አስተሳሰብ
             ልንቃኘው ይገባል።






                                                                        69
   72   73   74   75   76   77   78   79   80   81   82