Page 75 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 75
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
ከዚህ በላይ በአጭሩ የተጠቀሱት ሃሳቦች እንደሃሳብ እንከን ሊወጣላቸው
የማይችል ከመሆናቸውም ባሻገር፣ በወቅቱ በፌደራል እና በትግራይ ክልል መንግሥታት
መካከል ከነበረው ውጥረት አኳያ፣ እኔን ጨምሮ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን
የሚጋሯቸው ጭንቀቶች እና ሃሶቦች ይመስሉኛል። ለዚህም ታላቅ ከበሬታ እና አድናቆት
ሊቸራቸው ይገባል። ይህ እንዳለ ሆኖ፣ የተለያዩ ወገኖች ወ/ሮ ሙፈሪያትን ከልዩ ልዩ
አቅጣጫ ሲወቅሱ ተሰምተዋል። ከዚህ በመቀጠል የነዚህን ወገኖች ዋና ዋና መከራከሪያዎች
ለመመልከት እንሞክራለን።
በቀዳሚነት በብዙዎቹ የተነሳው፣ እነኚህን ከብልፅግና ፓርቲ የተለዩ የሚመስሉ
ሃሳቦችን አደባባይ ላይ እንዲወጣ ማድረጋቸው ከፓርቲው መስመር ማፈንገጣቸውን
ከማመልከቱም በላይ በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መካከል መከፋፈል እንዳለ ያሳያል
የሚለው ነው። እንዲህ አይነቱ አመለካከት ለረጂም ዘመናት ተቆራኝቶን ከቆየው
የዴሞክራሲያዊ ማዕከላዊነት አስተሳሰብ ጋር የተያያዘ እና የውስጠ ፓርቲ ዲሞክራሲ
አስፈላጊነትን ካለመረዳት የመነጨ ሊሆን ይችላል። ከምህዳራዊ አስተሳሰብ አኳያ፣ ባንድ
ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ውስጥ በመሰረታዊ የፖለቲካ ዓላማዎች እና ግቦች የጋራ አመለካከት
መኖር አስፈላጊ የመሆኑን ያህል ወደነዚህ ግቦች ለመድረስ በሚያስችሉ መንገዶች ላይ
የተለያዩ አማራጮች መኖር ለፓርቲው ጤናማነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
ይህን መግለጫ እስከሰጡበት ጊዜ ድረስ፣ ብልፅግና ፓርቲ እንደ ፓርቲ በወቅቱ
በፌዴራል መንግስቱ እና በትግራይ ክልል መንግስት መካከል እየሰፋ የነበረውን
የአመለካከት እና የአስተዳደር ልዩነት ከጦርነት እና ግጭት በመለስ መፈታት እንደሚገባው
ይገልጽ ነበር። በርግጥ፣ ከብልፅግና ውጭ ያሉ አንዳንድ ፖለቲካኞች እና ተንታኞች
የትግራይ ክልልን በመምራት ላይ የነበረው ህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት)
በማናቸውም መንገድ ከስልጣን እንዲወገድ የሚሹ እንደነበር አይካድም። በብልፅግና ፓርቲ
ውስጥም ይህንን አማራጭ የሚደግፉ ወገኖች እንደነበሩ ይገመታል። ይህ እንዳለ ሆኖ፣
ችግሮችን በልዩ ልዩ አማራጮች የመፈተሽ እና የማንሸራሸር ባህል ለሃገሪቱ ፖለቲካ
ጤናማነት የሚበጅ እንጂ ጎጂ ተደርጎ መወሰድ አልነበረበትም። በመሆኑም፣ ብልፅግናም ሆነ
ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ለየት ያሉ ሃሳቦችን ወደ አደባባይ ማውጣት ሊያበረታቱት
የሚገባ ልማድ ነው። ከሁሉም በላይ ግን ሊታመን የሚገባው፣ የፖለቲካ ልዩነቶችን
በሰላማዊ መንገድ መፍታት የምንጊዜውም ተመራጭ መንገድ መሆኑን ነው።
በሁለተኛ ደረጃ የሚነሳው፣ እንዴት በማናቸውም መንገድ ከኢትዮጵያ የፖለቲካ
28
ሥርዓት መወገድ ከሚገባው ህወሃት ጋር ባንድ ጠረዼዛ ዙሪያ ቁጭ ብለን እንወያይ ይላሉ
የሚል ነበር። እነኚህ ወገኖች፣ ባብዛኛው በህወሃት የበላይነት ይመራ በነበረው ዘመነ
28 የዚህ መጽሃፍ ዝግጅት እየተጠናቀቀ ባለበት ወቅት፣ የትግራይ ህዝብ ነፃአውጭ ግንባር ከህጋዊ
ድርጅትነት መሰረዙን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያስታወቀ ቢሆንም ተመሳሳይ ስህተቶች ወደፊት
እንዳይደገሙ ከነበረው ሁኔታ መማር ጠቃሚ ነው።
67