Page 87 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 87
ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ
6.2 ከተዓብዮ ወደ ዓይነታዊ የለውጥ ተረክ ለመሻገር
ከላይ እንደተጠቀሰው፣ በማናቸውም ሃገረ መንግስት ታሪክ ውስጥ፣ የተለያየ
ይዘት ያላቸው ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ተረኮች (narratives) መኖር
የሚጠበቅ ሲሆን ይህ በራሱ ለግጭት የሚያበቃ አይደለም። ተረኮች ወደ ግጭት
የሚያመሩት አንደኛው ወገን በራሱ ተረክ በመታበይ የእኔ የሚለውን ተረክ በሌላው ላይ
በኃይል ለመጫን በሚሞክርበት ወቅት ነው። ከ1950ዎቹ ጀምሮ፣ በሃገራችን ለተከሰቱት
የፖለቲካ ግጭቶች እና የርስ በርስ ጦርነቶች ዋነኛው መነሻም በእንደዚህ አይነት መታበይ
የአንድ ወገን ተረክን በሌላው ላይ ለመጫን ከሚደረግ ጥረት ጋር የተያያዘ ነው።
በምህዳራዊ አስተሳሰብ መሰረት፣ በማናቸውም ህብረተሰብ ውስጥ የሚገኙ
ተቃራኒ ተረኮችን (conflicting narratives) ወደ ዐይነታዊ የለውጥ ተረክ
(transformational narratives) ማምጣት ያንን ማህበረሰብ በዘላቂነት ወደፊት
ለማሻገር ቁልፍ እና አይነተኛ እርምጃ ነው። ይህ በሰላማዊ ሂደት መሆን በማይችልበት
ጊዜ፣ የምህዳሩ በከፍተኛ ቀውስ መናጥ ሌላኛው ነባሪ አማራጭ (default option)
ይሆናል። አብዛኞቹ ግጭቶች እና ጦርነቶች የአንዲህ ዓይነት አማራጮች ውጤቶች
ናቸው። ይህንን ተከትሎም ቀውሱን ለመሻገር የሚያስችል የስክነት እና አስተውሎት
ተዋናዮች መኖር እጅግ አስፈላጊ ይሆናል። ባለፉት ሶስት ዓመታት፣ በህወሃት እና በለውጡ
ኃይል መካከል መሰረታዊ የሆነ ሃገራዊ የፖለቲካ ተረክ ልዩነት የነበረ መሆኑ የአደባባይ
ሚስጥር ነው። በመጨረሻም፣ የህወሃት ተዓብዮ ከልኬቱ አልፎ በሃገር መከላከያ ሰራዊት
ላይ በወሰደው አሳፋሪ እርምጃ ሀገሪቱን አሳዛኝ ለሆነ የጦርነት ፍዳ ሊዳርጋት በቅቷል።
በሰሜኑ የሃገራችን ክፍል የተካሄደው ህግ የማስከበር ዘመቻ መጠናቀቁን
ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓብይ አህመድ ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት
ማብራሪያ ሃገራችን የምትገኝበትን ልዩ የታሪክ አጋጣሚ ያመላከተ ነበር። የገባንበት ቀውስ
ለሁላችንም ግልጽ ስለሆነ፣ በዚህ ክፍል የተጋፈጥነው ቀውስ የፈጠራቸውን መልካም
አጋጣሚዎች በመጠቀም እንዴት ለዘላቂ ሃገራዊ ልማት ወደሚጠቅም ዓይነታዊ የለውጥ
ተረክ መሸጋገር እንደሚቻል ለመጠቆም ይሞከራል።
ዓይነታዊ የለውጥ ተረኮችን ለማበልጸግ በስራ ላይ ከሚውሉት መርሆዎች አንዱ
እና ዋነኛው፣ በልዩ ልዩ ምክንያት አወዛጋቢ እና አጨቃጫቂ የሆኑ ጉዳዮችን ለቀጣይ
ሂደት በማቆየት፣ አብዛኛውን ወገኖች ሊያግባቡ በሚችሉ ዋና ዋና ሰበዞች ላይ ተመርኩዞ
የጋራ ሃገራዊ ራዕይ መስረቶችን ማጠናከር ነው። ይህንን በጽንሰ ሃሳብ ደረጃ ከማብራራት
ይልቅ ከአንዳንድ ስሞናዊ ሁነቶች ጋር በማያያዝ መመልከት ይቻላል።
ከነዚህም የመጀመሪያው፣ የሃገር መካላከያ ሰራዊቱ እና ክልላዊ ሃይሎች በሃገሪቱ
አጠቃላይ ህልውና ላይ የተጋረጠውን አደጋ ለመመከት ያደረጉት ተጋድሎ እና የትግራይ
ህዝብን ጨምሮ መላው የሃገሪቱ ህዝብ ያሳየው የሰላም እና ሃገር ወዳድነት ስሜት ተጠቃሽ
ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ፣ ጦርነቱን ተከትሎ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተወካዮች ምክር ቤት
79