Page 40 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 40

ደስታ መብራቱ



                  ተመክሮአዊ መማማር (adaptive  learning)፡  በዚህ  መርህ  መሰረት፣

           ውጤታማ ተመክሮአዊ የመማማር ስርአት ያለው ምህዳር ያልተቋረጠ እና ቀጣይነት ያለው
           ሽግግር  ለማረጋገጥ  ከፍተኛ  አቅም  ይኖረዋል።  ይህም  ማለት፣  ጠቃሚ  መረጃዎችን
           በስርዓት  የሚያደራጅ፣  የሚያጠራቅም  እና  ካንድ  ትውልድ  ወደ  ሌላው  ትውልድ
           የሚያሸጋግር ምህዳር ላልተቋረጠ እና ቀጣይ ለሆነ ሽግግር ጥሩ መሰረት ይኖረዋል። እዚህ
           ላይ፣ ማንኛውም አይነት የፖለቲካ ምህዳር፣ የመጠኑ መብዛት እና ማነስ እንደተጠበቀ
           ሆኖ፣ የራሱ የሆነ መልካም እና ጎጂ ጎኖች ሊኖሩት እንደሚችሉ መረዳት ያስፈልጋል።
           እንዳለመታደል  ሆኖ፣  የዘመናዊ  ፖለቲካ  ታሪካችን  በአብዛኛው  የነበረውን  ከመሰረቱ
           አፍርሶ እንደ አዲስ የመጀመር በሽታ የተጠናወተው ነው።

                  ቀደም ሲል እንደተጠቀሰው፣ ሃገር በቀል የእውቀት ስርአቶች በትውልድ የዳበሩ
           ጠቃሚ መረጃዎች በማከማቸት እና ለቀጣይ ትውልድ በማሸጋገር ከፍተኛ ድርሻ አላቸው።
           ነገር ግን፣ የሃገራችን የፖለቲካ ባህል ሃገር በቀል እውቀቶችንም ሆነ ጠቃሚ የፖለቲካ
           ተመክሮዎችን ባግባቡ አድራጅቶ በመጠቀምም ሆነ ለተተኪው ትውልድ በማስተላለፉ
           ረገድ ከፍተኛ ድክመት ያለበት ነው። ይህንን ችግር ለማስወገድ፣ አንጋፋ ፖለቲከኞቻችን
           ካለፈው ትውልድ በጎም ሆነ ክፉ ተመክሮዎች ልንማር የሚገባንን በቅንነት በማስተማር፤
           ወጣት የፖለቲካ  መሪዎቻችንም በበጎው  ተመክሮ ላይ  ለመገንባት እና ጎጂ ታሪካችንን
           ላለመድገም ብርቱ ጥረት ማድረግ ይኖርባቸዋል።
                  በአጠቃላይ፣ ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት መርሆዎች በተቀናጀ መልኩ ከተተገበሩ፣
           ቀደም  ሲል  የተጠቀሱትን  መሰረታዊ  የፖለቲካ  ህመሞቻችንን  በማከም  የወደፊቱን
           የሃገራችንን የፖለቲካ ምህዳር በጤናማ መሰረት ላይ ለመገንባት ያግዛሉ ተብሎ ይታመናል።
           ለዚህም ተግባራዊነት፣ የፖለቲካ መሪዎች፣ ምሁራን፣ አንቂዎች እና ተንታኞች ጥልቀት እና
           ብስለት በሚጎድላቸው አመለካከቶች ላይ ተመርኩዞ ህዝብን፣ በተለይም ወጣቱን ትውልድ
           ስሜታዊ ለሆነ እንቅስቃሴ ከማነሳሳት ሊቆጠቡ ይገባል።
           የክፍል ሁለት ቁልፍ ሃሳቦች

              i.   ምህዳራዊ  አስተሳስብ  ለትንተና  ከሚጠቀምባቸው  ተምሳሌታዊ  የተፈጥሮ
                  ክስተቶች  አንደኛው  የበረዶ  ቋጥኝ    (Iceberg)  ተምሳሌታዊ  ትንታኔ  ነው።
                  አብዛኛዎቹ በውቅያኖስ ውስጥ የሚገኙ የበረዶ ቋጥኞች አብዛኛው አካላቸው
                  በውሃው ተሸፍኖ ከውሃው ጠለል በላይ የሚታየው አካላቸው እጅግ በጣም
                  አነስተኛው ነው። በዚህም የተነሳ፣ በርካታ የባህር ልምዳቸው አነስተኛ በሆኑ
                  ካፒቴኖች የሚመሩ እና በአካላዊ ታላቅነታቸው አይደፈሩም ተብለው የታመኑ
                  መርከቦች ፍጻሜአቸው አሳዛኝ ሆኗል።
             ii.   አንድን የፖለቲካ ምህዳር በምህዳራዊ ትንተና መነጽር ስንመለከት አራት አበይት
                  ክፍሎች እናገኛለን። የመጀመሪያው ከማንኛውም ሰው የዕለት ተዕለት ህይወት
                  ጋር  በቀጥታ  ወይንም ቀጥተኛ ባልሆነ መንገድ የተያያዙ እና በቀላሉ ሊታዩ
                  የሚችሉ ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁነቶች (events) ናቸው። ሁነቶችም ሆኑ
   35   36   37   38   39   40   41   42   43   44   45