Page 18 - ምህዳራዊ አስተሳሰብ፣ ለዘላቂ ሃገራዊ መፍትሔ Final
P. 18

ደስታ መብራቱ


                  ሃያኛው ክፍለ ዘመን፣ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ የሳይንስ
           እና ቴክኖሎጂ እድገት የተመዘገበበበት ዘመን መሆኑ ግልጽ ነው። በዚያው መጠን ግን፣
           በአጠቃላይ የሰው ልጅ ከተፈጠረበት ዘመን አንስቶ በተፈጥሮ አካባቢያችን  ላይ ከታየው
           ከባቢያዊ ለውጥ የገዘፈ ተጽዕኖ በምድራችን ምህዳር ላይ ባለፉት ሁለት መቶ ዓመታት
           አስከትሏል። በዚህም የተነሳ፣ ዓለማችንን በመሰረታዊነት ሊቀይራት ወደሚችል ፍጹም
           የሰው ልጅ ጭፍን የበላይነት ዘመን (the Anthopocene age) እንደገባን የሚያሳዩ በርካታ
           ሳይንሳዊ መረጃዎች በመውጣት ላይ ይገኛሉ። ይህ ሁኔታ በዚሁ ከቀጠለ፣ የዓለማችን
           ከባቢያዊ መዛባት ብቻ ሳይሆን የሰው ልጅም እንደፍጡር መቀጠል (existential) ፈተና
           ውስጥ ሊገባ እንደሚችል ይገመታል።

                  ባለፈው  አንድ  ዐመት  ውስጥ  የተከሰተው  የኮሮና  ቫይረስ  እና  በዓለማችን
           ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ህይወት ላይ ያስከተለው ቀውስ ሊከተል ስለሚችለው ጥፋት ጥሩ
           የማንቂያ  ደወል  ሊሆን  ይችላል።  ይህንን  በይበልጥ  ለመረዳት፣  በቅርቡ  የተባበሩት
           መንግስታት  የልማት  ፕሮግራም  ያወጣውን  የዚህን  ዓመት  የሰዎች  ልማት  ሪፖርት
           (Human Development Report 2020) መመልከት ጠቃሚ ይሆናል። በሃያኛው ክፍለ
           ዘመን  የታየው  ፈጣን  የኢኮኖሚ  ዕድገት  በተፈጥሮ  ከባቢያችን  ላይ  ካስከተለው  ጎጂ
           ተጽዕኖዎች ባሻገር፣ በቢሊዮን የሚቆጠሩ የዓለማችን ህዝቦችን የስራ እና የመኖር ዋስትና
           አሳጥቷል።  ይህም፣  በመላው  ዓለም  ዙርያ  የፖለቲካ  አለመረጋጋቶችን  እና  ህዝባዊ
           ተቃውሞዎችን  አስከትሏል።  በዚህም  የተነሳ፣  ዛሬ  በዓለማችን  ገኖ  ያለው  ኢዘላቂ
           (unsustainable) የዕድገት እና ልማት አቅጣጫ በመሰረታዊነት ካልተቀየረ በመጪዎቹ
           ዓስርተ ዓመታት የሀገሮች እና ህዝቦች ፈተና ይበልጥ እየተጠናከረ እንደሚሄድ ይገመታል።
   13   14   15   16   17   18   19   20   21   22   23