Page 4 - Ayinie Magazine
P. 4

መልዕክት
                                                    የዓይን ባንክ አገልግሎት በዓለም ላይ ከተጀመረ የአንድ ሰው አማካይ
                                                    ዕድሜ እንኳን አልሞላውም፡፡ 70 ዓመት እንኳን በቅጡ አልሞላውም፡
                                                    ፡ ግን አድጓል - ጎልብቷል፡፡ የብሌን ንቅለ ተከላ በዓይን ህክምና ተቋማት
                                                    ከተጀመረ ግን አንድ ክፍለ ዘመን ሊሆነው ነው፡፡ የብሌን ንቅለ ተከላ
                                                    መጀመርን ተከትሎ የተጀመረው የዓይን ባንክ አገልግሎት ከአሜሪካ
                                                    ተነስቶ አውሮፓን አዳርሶ እስያ ጎልምሷል፡፡ አፍሪካ ውስጥ ግን ገና ልጅ
                                                    ነው - ወደ ወጣትነት የቀረበ፡፡

                                                    በአህጉራችን  አፍሪካ  እንደ  ኢትዮጵያ  የዓይን  ባንክና  እንደ  ደቡብ
                                                    አፍሪካው የዓይን ባንክ ከአስር ዓመታት በላይ ቋሚ አገልግሎት እየሰጠ
                                                    የቀጠለ የለም፡፡ ይጀመራሉ - ወዲያው ይከስማሉ፡፡ የኢትዮጵያ የዓይን
                                                    ባንክ ግን እነሆ ሰኔ 2009 ዓ.ም 14 ዓመት ሆነው፡፡
                                                    በአፍሪካ ውስጥ የአካልና ህዋስ ልገሳ አለመጎልበት የሚፈጥረው ችግር
                                                    ለዓይን ባንኮች ህልውናቸውን የሞትና የህይወት ጉዳይ አድርጎባቸዋል፤
                                                    በስልጣኔ  ያደጉት  የምዕራቡ  ዓለም  ዓይን  ባንኮች  ቀድመው
                                                    መጀመራቸው  የህዝባቸውን  ግንዛቤ  እንዲለውጡ  አስችሏቸዋል፤
                                                    እስያዎቹም  ከአፍሪካ  በሚሻል  ሁኔታ  ላይ  ናቸው  -  ህንድና  ኔፓል
                                                    ደግሞ ለዚህ ማሳያ ናቸው፡፡
                                                    የኢትዮጵያ  የዓይን  ባንክ  ሲጀመር  በሁሉም  ዘንድ  ስጋት  ነበር  -
                                                    በባለሙያውም  በህብረተሰቡም፡፡  የብሌን  ልገሳ  ማግኘት  ከባድ  ሆኖ
                                                    ይቀጥላል  ቢባልም  እነሆ  ለውጦች  እየታዩ  ከ1600  በላይ  ወገኖች
                                                    በንቅለ ተከላ ብርሃን ማግኘት ችለዋል፡፡ ከትናንት ዛሬ ይሻላል ፤ ነገ
                                                    ደግሞ የበለጠ ጥሩ እንደሚሆን እናምናለን፡፡

                                                    ዓይን ባንኩ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ከመለወጥ ጎን ለጎን ዓለም አቀፍ
                                                    የዓይን ባንክ ጥራት ስታንዳርዱን እንደጠበቀ መጓዝም ይጠበቅበታል፡
                                                    ፡ በዚህ ዓመትም የጥራት ምስክር ወረቀት ለማሳደስ የጥራት ኦዲት
                                                    የምናስደርግበት ጊዜ ነው፡፡ ይህ የዓይን ባንኩ ሌላው የህልውና ጉዳይ
                                                    ነው፡፡ ለማሳካትም ጠንክረን እየሰራን እንገኛለን፡፡
         ዶ/ር መነን አያሌው                               የባለሙያዎቻችንን  አቅም  ማጎልበትና  አዳዲስ  ብቁ  ሰራተኞችን

                                                    የማሟላት  ጉዳይም  አንዲሁ  የትኩረት  አቅጣጫችን  ነው፡፡  በዚህ
           የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ                          ረገድም የቴክኒካል ሱፐርቫይዘርን ጨምሮ የዓይን ባንክ ቴክኒሻኖችንና
            ሜዲካል ዳይሬክተርና                            የብሌን ልገሳ አማካሪዎችን ቅጥር ፈፅመናል ፤ ስልጠና በመስጠትና
                                                    ልምድ  በማካፈልም  ዘርፉን  እንዲቀላቀሉ  ተደርጓል፡፡  በቀጣይነት
            የባለአደራ ቦርድ ፀሐፊ                          የባለሙያዎችን አቅም ማጎልበት ተጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል፡፡

                                                    በፋይናንስ፣ በአደረጃጀትና በዓለም አቀፍ ግንኙነት ረገድ የሚጠበቁብንን
                                                    ስራዎችም  በስፋት  የምንተገብራቸው  ይሆናል፡፡  ስለሆነም      ዓይን
                                                    ባንኩ የህዝብ ነውና ሁላችሁም በገንዘብ፣ በዕውቀት፣ በማቴሪያልና
                                                    በሌሎችም ድጋፍ በማድረግ ጥረቱን እንድታግዙ ጥሪዬን አቀርባለሁ ፤
                                                    አመሰግናለሁ!!

             2
   1   2   3   4   5   6   7   8   9