Page 5 - Ayinie Magazine
P. 5

መልዕክት
              የኢትዮጵያ  የዓይን  ባንክ  ሲቋቋም  ዋኛ  ዓላማው  በብሌን  ጣባሳ
              ምክንያት  ዓይነ  ስውር  የሆኑ  ዜጎቻችን  መልሰው  ብርሃን  እንዲያገኙ
              ለማስቻል  ከህልፈት  በኋላ  ከለጋሽ  ወገኖች  ብሌን  በማሰባሰብ፣  ጥራቱንና
              ደህንነቱን ጠብቆ ለንቅለ ተከላ ህክምና እንዲያሰራጭ ነው፡፡  ከተመሰረተበት
              ጊዜ አንስቶ እስከ ሚያዝያ 2009 ድረስ ከ1600 በላይ ወገኖች በተለያዩ
              የህክምና ማዕከላት የብሌን ንቅለ ተከላ ተከናውኖላቸው ብርሃን አግኝተዋል
              ፤ ከ15 ሺህ በላይ ወገኖችም ከህልፈት በኋላ ብሌን ለመለገስ የቃል ኪዳን
              ሰነድ ላይ ፈርመዋል፡፡

              በምስረታው ወቅት አንድ የንቅለ ተከላ ስፔሻሊስትና አንድ ቴክኒሻን ብቻ
              የነበረው በአሁኑ ወቅት 10 የብሌን ንቅለ ተከላ ስፔሻሊስቶች ደርሰዋል፤
              ሶስት  ቴክኒሻኖች፣  6  የብሌን  ልገሳ  አማካሪዎችና  ሌሎች  ድጋፍ  ሰጪ
              ሰራተኞች  ባለቤት  ሆኗል፡፡  የተሟላ  የዓይን  ባንክ  ላብራቶሪና  የስራ
              መሳሪያዎችም ባለቤት ሆኗል፡፡
              ባለፉት ጊዜያት በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል ብቻ ይሰራጭ የነበረው ብሌን
              አሁን አዲስ አበባ በዳግማዊ ምኒልክ ሆስፒታል፣ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣
              በብሩህ  ቪዥን  ከፍተኛ  የዓይን  ክሊኒክ፣  በዋጋ  ቪዥን  ከፍተኛ  የዓይን
              ክሊኒክ፣ በፍፁም ብርሃን የዓይን ክሊኒክ እንዲሁም በክልሎች በአማራ
              ክልል በጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል፣ በኦሮሚያ ክልል በጅማ ዩኒቨርሲቲ
              ሆስፒታል፣ በትግራይ ክልል በኩዊሃ ሆስፒታል እና በደቡብ ክልል በሀዋሳና
              አርባምንጭ  ዩኒቨርሲቲ  ሆስፒታሎች  ለስፔሻሊስት  ዶክተሮች  በማቅረብ
              ታካሚዎች በሚቀርባቸው ቦታ ንቅለ ተከላ እንዲደረግላቸው ተመቻችቷል
              - ይህም አኩሪ ተግባር ነው፡፡

              ዓይን  ባንኩ  በአካልና  ህዋስ  ንቅለ  ተከላ  በአገራችን  ፈር  ቀዳጅ  ተቋም
              እንደመሆኑ  በአህጉራችን  ከአስር  ዓመታት  በላይ  አገልግሎት  ሳያቋርጥ
              የቀጠለና ዕድገት እያስመዘገበ ያለ ድርጅት ነው፡፡ አሰራሩም ዓለም አቀፍ
              የጥራት ደረጃን እንዲያሟላ ተደርጓል፤ በአሜሪካው ሳይት ላይፍ የጥራት
              ማረጋገጫ ተሰጥቶታል - ይህ ደግሞ የበለጠ ደስ ያሰኛል፡፡

              ባለፉት  14  ዓመታት  እነዚህና  መሰል  ዕድገቶች  የመኖራቸውን  ያህል  ግን
              አሁንም  ያልተሻገራቸው  ተግዳሮቶች  ብዙ  ናቸው፡፡  በሚኒስቴር  መስሪያ
              ቤታችን ቀደም ብሎ  በተደረገ ጥናት ከ300,000 በላይ የብሌን ጠባሳ
              ዓይነስውራን ይገኛሉ፡፡ እነዚህ ወገኖች ብርሃን እንዲያገኙ ለማስቻል ብዙ                     ዶ/ር ዳንኤል ገ/ሚካኤል
              መስራትን ይጠይቃል፤ በፋይናንስ፣ በሰው ሀይል፣ በቢሮ ግንባታና አደረጃጀት
              መሻሻል  የሚገባቸው  ጉዳዮች  ብዙ  ናቸው፡፡  ከዚህ  አኳያ  ጤና  ጥበቃ
              ሚኒስቴር አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ የሚያደርግ ሲሆን የባለአደራ ቦርዱና                             የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ
              አጋር አካላትም ከዓይን ባንኩ አመራሮችና ሰራተኞች ጋር በቅንጅት ጠንክረው                         የባለአደራ ቦርድ ሰብሳቢ
              መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡ ህብሰረተቡና ድርጅቶችም ይህንን የህዝብ ባንክ
              በተለያየ  መልኩ  መደገፍ  አገራዊ  ግዴታቸው  መሆኑን  በመገንዘብ  ከጎኑ                 በጤ/ጥ/ሚ የሚኒስትር ዴኤታ ፅ/ቤት ሀላፊ
              እንዲቆሙ ጥሪዬን አቀርባለሁ፡፡
              የኢትዮጵያ የዓይን ባንክ በአሰራሩና ጥራቱ በዓለም ተወዳዳሪ የሆነውን ያህል
              ያሉበትን  ተግዳሮቶች  ተወጥቶ  በብሌን  ማሰባሰብና  ማሰራጨት  ብዛትም
              ቀዳሚ እንዲሆን ምኞቴ የላቀ ነው፡፡ አመሰግናለሁ!


                                                                                                        3
   1   2   3   4   5   6   7   8   9   10