Page 90 - DINQ MAGAZINE OCTOBER 2020 EDITION
P. 90

ፍልስፍና










     “የአንዲት ወፍን እምነት ለማግኘት ዛፍ መሆን እመኛለሁ...”




        በሚስጥረ አደራው



       “የአንዲት ወፍን እምነት ለማግኘት ዛፍ                መፈራረቅ ፤ በመፈረረቅ ውስጥም ያለውን              የሚያስተሳስረን፤በደስታ ብዛት
       መሆን እመኛለሁ “ ያለውን ባለቅኔ ዛሬ ነበር            የመጠለውግና የመለምለምን አይታለፌነት               የማይነቀል፤ በሀዘን ጊዜ
       ማግኝት!                                   ያለምንም ማስተባበል ለሚመለከተው ሁሉ               የማይልፈሰፈስ፤በማግኝትም ሆነ በማጣት
                                               ያስተዋውቁታል። እኒህ ዛፎች በጋ መጥቶ              ወራቶች ቀጥ ብለን እንድንቆም
       “መጽሀፍ አንብቤ እፎይ ባልኩኝ ሰዓት
                                               ቅጥላቸው ሲለመልምም ሆነ፤ ክረምት                 የሚያስችለን ግንድ ሊኖረን ይገባል። የኑሮ
       ምነው ዛፍ በሆንኩኝ፤እያልኩ እመኛለሁ                 መጥቶ ቅጠላቸው ሲረግፍ፤ በተመሳሳይ                ቅርንጫፎችን ተሸኽሞ መቆም የሚችል
                                               ጽናት ስራቸው ሳይላላ ሁለቱንም ወቅቶች              ግንድ። በዚህ የማንንነት ግንድ ላይ ነው፤
       ወይ ፍሬ አፈራለሁ
                                               ቀጥ ብለው በጽናት ይሳልፋሉ። ይህንን ሳይ            ቅርንጭፎች ተፈጥረው የረገፉት ቅጥሎች
       ወይ ጥላ እሆናለሁ                             ነበር እንደ ዛፍ መሆንን የተመኝሁት። ከዚህ           መልሰው የሚያቆጠቁጡት። በክረምት
                                               የመፈራረቅ ስርዓት ማንም የአለም ፍጡር              የሚራቆተው ዛፍ የራሱ የሆነ ውበት
       ቢያንስ አንዲት ወፍ በግል አምና ጎጆ ቤቷን፤            አያመልጥምና። ይህንን መፈራረቅ በጥበብ              እንዳለው ሁሉ፤ በፈተና ወቅት የሚኖረን
       እንደምትሰጠኝ እተማመናለሁ ያኔ በትክክል               በማለፉ ረገድ ግን ሰው ያልሆኑት ፍጥረቶች            ማንነትም የራሱ ሆነ ውበት አለው። ይህ
       ለአደራ እበቃለሁ”- ነብይ መኮንን/ስውር               ሳይሻሉ አይቀርም።                           ውበታችን የሚወጣው ግን፤ ያለንበትን
       ስፌት                                                                           ወቅት አምነን መቀበል ስንችል ብቻ ነው።
                                               ማጣትን እንደዛፍ በጽናት ማለፍ ለሰው
       ሰሞኑን በምኖርበት ከተማ ዛፎች                     ይከብዳል። ሁሌም አረንጓዴ ለብሰን መኖር             እላያችን ላይ ያሉት ቅጠሎች በረገፉ ቁጥር
       ቅጠላቸውን የሚያጡበት ወቅት ነው።                   መብታችን ስለሚመስለን ክረምት መጥቶ                የሚደነግጥ ማንነት ሲኖረን ግን፤
       ላለፉት ወራቶች አረንጓዴ ለብሰው በኩራት               ቅጥላችን መቅላት ሲምጀር አንገታችንን               የመለምለሚያው ወቅት ሳይደርስ ግንዱ
       ቆመው የነበሩት ዛፎች በነዚህ ወራቶች                 እንደፋለን። የሚያልፍ አይመስለንም።                እራሱ ይወድቃል። በወደቀ ግንድ ላይ
       ቅጠላቸው ጠውልጎ ቀስ እያለ ከላያቸው ላይ              አሁን እየሆነው ያለው ነገር ሁሉ መጭውን             ደግሞ ምሳር እንጂ ህይወትን
       ይረግፋል። በርግጥ ለተመልካች ይህ                   ወቅት እንድናልፈው እያዘጋጀን መሆኑን               የሚያስቀጥሉ ቅጠሎች አይበቅሉም።
       የሚረግፈው ቅጥል እራሱ ውብ መልክ                   መረዳት ይከብደናል። ሁሉም ነገር                  ታዲያ ለምንድን ነው የነብዩ መኮንን
       አለው። ግን ደግሞ አረንጓዴ ለብሶ ያየነው              በቅጽበት እየሆነ በምናይበት አለም                 ግጥም ሽው ያለኝ? እራስ ወዳድነቴን
       ዛፍ እራቁቱን ቅርንጭፉን አንጭብርሮ ቆሞ               ውስጥ፤ትዕግስት ፈታኝ ባህሪ ነው።                 በትንሹ ስላሳየኝ። ባለቅኔው ዛፍ መሆንን
       ሲታይ ያሳዝናል። ተመልሶ ቅጠል የማያበቅል              እንደዛፍ ቅጠል ከላያችን ላይ በቅለው
       ይመስል ይራቆታል። እውነት ለመናገር                  ግርማ የሚሰጡን ብዙ አይነት ሰወኛ                 ሲመኝ፤ ከራሱ አልፎ ለሌሎች ጥላ
       እስከዛሬ ዛፎች በዚህ ወራት ለምን                   ቅጠሎች አሉ። ምናልባት ዛሬ ላይ አረንጓዴ            ለመሆን ነበር። ቢያንስ የአንዲትን ወፍ
       ቅጠሎቻቸው ይረግፋል ብዬ አጥብቄ ጠይቄ                ሆነው ይታዩ ይሆናል። ቁመናችንን                  እምነት ሲጠይቅ፤የገዘፈ ሰብዓዊነቱን
       አላውቅም ነበር፤ሆኖም ዛሬ በዚህ ላይ                 አሳምረው፤ በሰው ፊትም አግዝፈውን                 ያሳያል፤እኔ ዛሬ ላይ ሆኜ ዛፍነትን ስመኝ
       የተጻፉ ጽሁፎችን ሳይ ዛፎች ቅጠላቸውን                ይሆናል። የአረንጓዴነትን ውበት ማንም               በፍጹም እራስ ወዳድነት ነው። እሱ
       የሚያረግፉት መጭውን ቀዝቃዛ ወራቶች                  አያጣውም። ነገር ግን ወቅት ሲቀየርስ?              ለሌሎች ማረፊያነት ህሊናውን ሲያሰናዳ፤
       በህይወት ለማለፍ ሲሉ ነው።                       የነበረንን ስናጣስ?ያሳመረን ነገር ሲረግፍ፤           የእኔ ህሊና እስካውን እራሴን ለማዳን ነው

       እንደነዚህ አይነት ዛፎች አሁን ቅጠላቸውን              እራቁት የመሆን ጊዜ ሲመጣ፤ እንደ ዛፍ              የሚሮጥው። ይፈረድብኛል? ለሌሎች
       ካረገፉ በቂ ውሃና በቂ ጉልበት ሰብስበው               ግንድ የማይደነግጥና ሳይውድቅ                    ጎጆ  መስሪያ ከመሆን በፊት ጸንቶ መቆም
       መጪውን እጅግ ቀዝቃዛ የሆነ ክረምት                  ቀዝቃዛውን ወራት የሚያሳልፈን ማንነት               ይቀድማል! ጽኑ ዛፍ ብቻ ነው የወፊቱን
       በጽናት ማለፍ ይችላሉ። ቅጠላቸው ስለረገፈ              አለን? ይህ ይመስለኛል እራሳችንን                 እምነት ማግኘት የሚችለው::
       አይሞቱም፤ ቅርንጫፋቸውን ሰብረው                    ልንጠይቅ የሚገባን ወሳኝ ጥያቄ።
       አንገታቸውን አይደፉም። የወቅቱን                    አንድ ከስራችንን ጋር





        90                                                                                  “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ”                                                          ድንቅ   መጽሔት -  ጥቅምት  2013
   85   86   87   88   89   90   91   92