Page 20 - DINQ MAGAZINE MARCH 2021 EDITION
P. 20

የአፄ ምኒልክ አዋጅ                         ማን እንደ ምኒልክ!!                         ፊታውራሪ ጌጃ ገርቦ
                       (አድማስ ሬድዮ)                          (አድማስ ሬድዮ)                              (አድማስ ሬድዮ)
                                                    የቀድሞው  የአሜሪካ  ፕሬዚዳንት
               አፄ  ምኒልክ  መስከረም  7  ቀን  1888   ጆንኦፍ ኬነዲ "በምድር ላይ ጀግና ጥራ ብትለኝ              በደቡብ  ኢትዮጵያ  የሀዲያ  ተወላጅ  እና
        ዓ.ም ከዚህ ቀጥሎ ያለውን የክተት አዋጅ በይፋ        ቀድሜ የምጠራው ንጉሥ እምዬ ምኒልክ ነው             ልቅቦ  ከተባለ    በሀዲያ  ውስጥ  ከሚገኝ    ጎሳ
        በነጋሪት አስነገሩ፡፡                        ፣ ደርባባ ደፋር ናቸው።                       የተገኙ ጀግና ናቸው፡፡

              ‹‹እግዚአብሔር  በቸርነቱ  እስካሁን               የነጭ  ቀኝ  ገዥን  በአፍሪካ  ምድር             ፊት አውራሪ ጌጃ በአደዋ ዘመቻ የአጤ
        ጠላትን  አጥፍቶ  አገር  አስፍቶ  አኖረኝ፡፡  እኔም   ያንበረከኩ  ቆራጥ  ሰው!  ኢትዮጵያውያን            ምኒልክን  መልዕክት  ተከትለው  ከሀዲያ  አከባቢ
        በእግዚአብሔር ቸርነት ገዛኹ፡፡ እንግዲህ ብሞት        ጀግንነታቸው  የሚመነጨው  ከሌላ  ሚስጥር            ወደ  5ሺ  ጦር  እየመሩ    በአድዋ  ጦርነት  በፊት
        ሞት  የሁሉም  ነውና  ስለ  እኔ  ሞት  አላዝንም፡፡   አይደለም ከእምዬ ምኒልክ ነው። ለዚህም አገሬ          አውራሪነት  ከዘመቱ  ጀግኖቻችን  መካከል  አንዱ
        ደግሞ  እግዚአብሔር  አሳፍሮኝ  አያውቅም፤          አሜሪካ  በክብር  እዚህ  ድረስ  ታሪካቸውን          ናቸው፡፡
        ወደፊትም  ያሳፍረኛል  ብዬ  አልጠራጠርም፡፡
                                             በሙዚየም አስቀምጣለች "በማለት ገልፀዋቸው
                                             ነበር።

                                                    የፈረንሳዊ የቀድሞው መሪ ዣክ ሺራክ
                                             "የት  አለ  ጀግና  ለዛውም  በአፍሪካ  ምድር
                                             ከንጉሥ እምዬ ምኒልክ በላይ ? " ሲሉ በጥያቄ
                                             መልክ     ማንም    ተወዳዳሪ     እንደለለቻው
                                             አስቀምጠው ነበር።

                                                    የሊቢያው  መሪ  ጋዳፊ  ከመኖሪያ
                                             ሰገነታቸው ባንዱ ክፍል የንጉሡ እምዬ ምኒልክ
                                             ፎቶ  ነበር  ከስሩም  "ታላቅ  ሰው  "  ይላል።
                                             በመላው  የአፍሪካ  ሃገራት  የንጉሡ  ምኒልክ
                                             ታሪክ ትልቅ የመንፈስ መነቃቂያ ነው።

        አሁንም     አገር    የሚያጠፋ፣     ሃይማኖት                                                 የሐበሻ  ጀብዱ  የተደበቀው  ማስታወሻ
        የሚለውጥ  ጠላት  እግዚአብሔር  የወሰነልንን                                               ላይ እንደሰፈረው ፊት አውራሪ ጌጃ ገርቦ በአድዋ
        ባሕር  አልፎ  መጥቷል፡፡  እኔም  ያገሩን  ከብት                                           እና  በማይጨው  የፀረ  ፋሺስት    ዘመቻ  ላይም
        ማለቅ  የሰውን  ድካም  አይቼ  እስካሁን  ዝም                                             ትልቅ  ሚና  ነበራቸው፡፡  በ  1888  ዓ.ም  በአድዋ
        ብለው  ደግሞ  እያለፈ  እንደ  ፍልፈል  መሬት                                             ጦርነት፣  በ1928  ዓ.ም  ጣሊያን  የቀድሞውን
        ይቆፍር ጀመር፡፡                                                                 የአድዋ  ሽንፈት  ለመቀልበስ  ኢትዮጲያን  ድጋሚ
                                                                                   በወረራት  ወቅትም  ፊት  አውራሪ  ጌጃ  የሀዲያን
               ‹‹አሁንም  በእግዚአብሔር  ረዳትነት                                             ጦር እየመሩ ዘምተዋል፡፡
        አገሬን  አሳልፌ  አልሰጠውም፡፡  የአገሬ  ሰው
        ካሁን  ቀደም  የበደልሁህ  አይመስለኝም፡፡                                                      ፊት  አውራሪ  ጌጃ  ገርቦ  በዚህ  መልክ
        አንተም  እስካሁን  አላስቀየምኸኝም፡፡  ጉልበት                                             የሀዲያን ጦር እየመሩ  የአድዋ ጉዞ እስከሚጀመር
        ያለህ  በጉልበትህ  ዕርዳኝ፡፡  ጉልበት  የሌለህም                                           ጦራቸውን  አሰልፈው  በአዲስ  አበባ  በጊዜአዊነት
        ለልጅህ፣  ለምሽትህ፣  ለሃይማኖትህ  ስትል                                                አርፈው ነበር፡፡
        በሐዘን ዕርዳኝ፡፡
                                                                                         አዲስ  አበባ  ገብተው  ጉዞ  ወደ  አድዋ
                ወስልተህ     የቀረህ    ግን    ኋላ                                         እስኪ  ጀመር  በጊዚያዊነት  ያረፉበት  አካባቢም
        ትጣላኛለህ፣  አልተውህም  ማርያምን  ለዚህ                                                ‹‹የጌጃ  ጦር››  ሰፈር  ይባል  ስለነበር  ከዚያን  ጊዜ
        አማላጅ የለኝም፡፡ ዘመቻዬም በጥቅምት ነውና                                                ጀምሮ  እስከ  ዛሬ  ድረስ  ይህ  አከባቢ  ጌጃ  ሰፈር
        የሸዋ  ሰው  እስከ  ጥቅምት  እኩሌታ  ድረስ               ምኒልክ ተወልዶ ባያነሳ ጋሻ ፣            በሚል ስያሜ ይጠራል፡፡
        ወረይሉ ከተህ ላግኝህ፤” አሉ፡፡                        ግብሩ እንቁላል ነበር ይሄን ጊዜ አበሻ!                         ወደ ገጽ  52  ዞሯል




       20                                                                               “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር ”                                                          ድንቅ   መጽሔት           መጋቢት 2013
   15   16   17   18   19   20   21   22   23   24   25