Page 87 - Dinq 215 December 2020_Neat
P. 87
ክገጽ 16 የዞር
ንብረት ዘርፈዋል፣ አውድመዋል ይላል የኮሚሽኑ ሪፖርት፡፡
‹‹ሳምሪ›› የሚባለው የወጣቶች ስብስብ በአንድ ቡድን በአማካይ
ከ20 እስከ 30 ወጣቶች በመሆን፣ በየቡድኑ በግምት ከሦስት እስከ
አራት በሚሆኑ መሣሪያ የታጠቁ ፖሊስና ሚሊሻዎች እየታጀቡ
ጭፍጨፋውን ሲፈጽሙ፣ በየመንገዱ መታጠፊያዎች አድፍጠው
ይጠባበቁ የነበሩት ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ደግሞ ከጥቃቱ ለመሸሽ
የሚሞክርን ሰው በተኩስ በመመለስ የአጥቂውን ቡድን ጭፍጨፋ
በቀጥታ ይፈጽሙና ያስፈጽሙ እንደነበር ተገልጿል፡፡
የኢሰመኮ ሪፖርት ከሞቱት ሰዎች ብዛትና በአቅም ማነስ ምክንያት
የቀብሩ ሥነ ሥርዓት ሦስት ቀናት መውሰዱን፣ ሰዎች በጅምላ
መቀበራቸውን፣ እንዲሁም በምርመራ ቡድኑ ጉብኝት ወቅት ገና
ያልተቀበሩ በመንገድ የወደቁ አስከሬኖችም እንዳሉም
ያመለክታል፡፡
በማይካድራ ከተማ የተፈጸመው ጥቃት ተራ ወንጀል ሳይሆን
የታቀደና በጥንቃቄ ተቀነባብሮ የተፈጸመ እጅግ ከፍተኛ የሰብዓዊ
መብቶች ጥሰት መሆኑን፣ አጥፊዎቹ ሆነ ብለው፣ አቅደውና
ተዘጋጅተው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በመግደላቸው የተጎዱትን
ማቋቋምና አጥፊዎች ለሕግ እንዲቀርቡ የኮሚሽኑ ሪፖርት
አሳስቧል፡፡
DINQ MEGAZINE December 2020 STAY SAFE 87