Page 137 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 137
አብን
በማድረግ ለቱሪስቶቹ ቀላልና ቀልጣፋ አገልግሎት
እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡
ከዓለምአቀፍ ቱሪዝም ጎን ለጎን የአገር ውስጥ
ቱሪዝምን ለማስፋፋት የኃይማኖት መዳረሻዎችን፣
በዓላትን፣ ባሕላዊ ትዕይንቶችንና ሌሎች የመዝናኛና
ተፈጥሯዊ የጉብኝት ስፍራዎችን የማልማትና
የማስተዋወቅ ሥራ ይሰራል፡፡
አዳዲስ መዳረሻዎችን በተመለከተ
በየተዋረዱ የቱሪስት መዳረሻ ባንክ (Tourist
Attraction Bank) በማዘጋጀት አዳዲስ የቱሪዝም
መስህቦችን ወደ ባንኩ በማስገባትና ደረጃ በደረጃ
በመለየት የማልማት ሥራ የሚሰራበት ሁኔታ
ይቋቋማል፡፡
አዳዲስ ባሕላዊ፣ ታሪካዊና ተፈጥሯዊ የመስህብ
ስፈራዎችን ብቁና ተወዳዳሪ የቱሪስት መዳረሻ
ለማድረግ በመለየት፣በማልማትና በማስተዋወቅ
የሚሰራበት ከዓለምአቀፍና አገራዊ የቱሪስት
መስህብ የደረጃ ልኬት (measurement
standards) ጋር የሚግባባ መመዘኛ መስፈርትን
በማዘጋጀት እንዲሰራ ይደረጋል፡፡
በተለይም በውኃማና ተራራማ አካባቢዎች ጎብኝዎች
የሚከውኗቸውን ተግባራት (Tourism Activities)
በማስፋትና አዳዲስ የቱሪዝም ምርቶችን (Tourism
135 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !