Page 140 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 140
አብን
ከውሳኔ ሰጭነት እስከ ጥቅም ተጋሪነት ድረስ
ኅብረተሰቡ የሚሳተፍቸው አሰራሮችና አደረጃጃቶች
እንዲኖሩ ይደረጋል፡፡ ይህም የባለድርሻ አካላት
ፎረም፣ምክር ቤትና ሌሎችን በማቋቋም ተግባራዊ
እንዲደረግ የሕግና መመሪያ ማዕቀፍ ይበጅለታል፡፡
በአካበቢው በሚሰሩ የልማት ሥራዎችና
ኢንተርፕራይዞች በልማት እራሱ ኅብረተሰቡ
አልሚ ሆኖ እንዲሳተፍ የሚስችሉ ዘርፎችም
ተለይተው ይሰራሉ፡፡
በባለኃበቶችና በውጪ ዜጎች በሚለሙ የቱሪዝም
ልማቶች ውስጥም ሕብረተሰቡ በቅጥር፣ግብዓት
በማቅረብና ሌሎች ተጓዳኝ አግልጎሎቶችን
ለድርጅቶች ለማቅረብ እንዲችል የሕግና መመሪያ፣
የመግባቢያ ስምምነቶችም በሚኖሩበት አግባብ
እንዲሰራ ሆኖ ይዘጋጃል፡፡
መ. የቅርስ፣ ጥብቅ ሥፍራዎች ጥበቃና አካባቢ
እንክብካቤን በተመለከተ
የቱሪዝም መዳረሻ አስተዳደራዊ እቅድ
(Destination Management Plan) እና
የወሰን ክልል (buffer zone) እንዲዘጋጅ
በማድረግ የሚሰራበት አግባብ በመፍጠር
ይሰራል፡፡
138 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !