Page 141 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 141
አብን
ከባሕልና ቱሪዝም እንዲሁም ከአካባቢ ጥበቃ
ተቋማት በተጨማሪ የቱሪስት መዳረሻ
የመስህብ ስፍራዎች የትስስር ፎረምና ምክር
ቤቶችን በማቋቋም ከልማቱና ገበያ ትስስሩ ጎን
ለጎን የጥበቃና እንክበካቤ ሥራው እንዲሰራ
ይደረጋል፡፡
በአገርና ክልል ደረጃ የአካባቢ እንክብካቤና ቅርስ
ጥበቃ ፈንድ (heritage protection and
environmental conservation fund)
በማቋቋም በዘላቂነት የጥበቃና እንክብካቤ
ሥራውን በገንዘብ ለመደግፍ የሚያስችል
ተቋማዊ አሰራር ይዘረጋል፡፡ አሁን ላይ
በከፍተኛ የኅልውና አደጋ ላይ ያሉት ላሊበላ፣
የጣና ኃይቅ እና ሌሎች ተመሳሳይ አደጋ
የተደቀነባቸው ብርቅዬ ቅርሶቻችን ጉዳይ
የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት የሚሰራ
ይሆናል፡፡ ይህን ጉዳይም በዋናነት ረጅ
ድርጅቶችን፣ባለሀብቶችንና ዲያስፖራውን
በማሳተፍና ከመንግስትም ተገቢውን በጀት
በመበጀት እንዲሰራ ይደረጋል፡፡
ችግሩ በሌሎችም ሀብቶቻችን ላይ ከፍተኛ ደረጃ
ከመድረሱ በፊት በተለያየ ጊዜ በተከፋፈለ
መደበኛ ጊዜ የዳሰሳና ጥልቅ ጥናት በማድረግ
ቀድሞ የመከላከል ሥራ እንዲሰራ የሚደረግበት
አሰራር ይዘረጋል፡፡
139 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !