Page 146 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 146

አብን


                            የእርምት እርምጃዎች የሚውሰዱበት የአሰራር

                            ሥርዓት ይዘረጋል፡፡

             አብን  ኢትዮጵያ  ያላትን  ሰፊና  እምቅ፤  ተፈጥሯዊና  ሰው
             ሰራሽ፤ባሕላዊና  ኃይማኖታዊ  እንዲሁም  ታሪካዊ  የቱሪዝም
             መስህቦች  በማልማት  ኃብቱን  ጠብቆና  ተንከባክቦ  ከትውልደ
             ወደ  ትውልድ  የማስተላለፍ  ኃላፊነት  በዛሬው  ትውልድ  ላይ
             የተጣለ  መሆኑን  በጥልቅ  በመረዳት  ሕዝቡ  በዘርፉ  ያለውን
             ፀጋ  ተጠቅሞ  መልማት፣  ከድህነት  የመውጣትና  የመዘመን

             እድሉን  ሁሉ  አሟጦ  እንዲጠቀም  ለማድረግ  በትኩረት
             ይሰራል፡፡  ከዚህ  ባለፈም  የቱሪዝሙን  ልማት  ከማምረቻ፣
             ግብርና እና ትራንስፖርት ዘርፉ ጋር ለማስተሳሰርና ለማዘመን
             በቴክኖሎጅ፣  በእውቀትና  በክህሎት  የተሻሉ  ባለሙያዎችን
             የማፍራት፣እቅም  የማሳደግና  በየጊዜው  ተገቢው  ቁጥጥርና
             ክትትል  የሚደረግ  ይሆናል፡፡ዘመናዊ  እና  ዓለምአቀፋዊ

             የቱሪዝም  ሥርዓትን  በጠበቀ  መልኩ  የማሻሻል፣  አዳዲስ
             የቱሪዝም  ምርቶችን  የማስተዋወቅና  ለገበያ  የማቅረብ፣  የገበያ
             ትስስር  የመፍጠርና  ተገቢውን  የእሴት  ሰንሰለት  (Value
             Chain)  መፍጠር  ትኩረት  የሚሰጣቸው  ሆነው  ይሰራሉ፡፡
             በዚህ  ሁሉ  ሂደት  ሌሎች  ባለድርሻ  አካላትና  የአካባቢው
             ማህበረሰብ  እና  ዲያስፖራዎች  በቱሪዝም  ዘርፉ  ልማት  ዙሪያ
             በንቃት  እንዲሳተፉ  በሰፊውና  በጥናት  ተመርኩዞ  እንዲሰራ
             ይደረጋል፡፡








             144    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   141   142   143   144   145   146   147   148   149   150   151