Page 150 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 150
አብን
requirement) ወዘተ ታሳቢ ባደረገ መንገድ መከናወን
አለበት፡፡
የውኃ ልማት ስራዎች የሴቶችን ልዩ ፍላጎትና ሁኔታ
ግምት ውስጥ ያስገባ እንዲሆን ይደረጋል፡፡
ድንበር ተሸጋሪ የውኃ ኃብቶችን አስተዳደርና የአገራችን
ያላትን ፍትኃዊ ተጠቃሚነት የማረጋገጥ፣ ተቋማዊ
በሆነ መንገድ አገራችን ከድንበር ተሸጋሪ ወንዞቿ
ፍትኃዊ የውኃ ተጠቃሚነቷን በሚያረጋግጥ መንገድ
የሚመራ ተቋም ይመሰረታል፡፡
በአገራችን እስከአሁን የተገነቡ ተቋማት ከፍተኛ የሆነ
የዘላቂነት (sustainablity) ችግር ያለባቸውና ከተገነቡ
የመጠጥ ውኃ ልማት ተቋማት ውስጥ እስከ 60 በመቶ
የሚሆን የብልሽት ወይም አገልግሎት አለመስጠት
መጠን (non functionality rate) ያለ ሲሆን ለዚህም
የውኃ መሰረተ ልማቶቻችን በደለል መሞላት፣ አስፈላጊ
የሆኑ የኦፕሬሽንና ጥገና ሥራዎች አናሳ መሆንና
የመለዋወጫ እቃዎች እንደ ልብ አለመገኘት ዋና
ዋናዎቹ ችግሮች ናቸው፡፡ ስለዚህ አብን ለሚገነቡ
የውኃ መሰረተ ልማቶች አስፈላጊ የሆነ የኦፕሬሽንና
ጥገና እቃ አቅርቦት ከቀረጥ ነጻ እንዲገቡ ያደርጋል፣
የተገነቡ ተቋማትም በአግባቡ እየተጠገኑ አገለግሎት
የሚሰጡበት ስልት ይቀየሳል፡፡
ከላይ ወደ ታች የሚወርድ የውኃ ኃብት ልማት
አቅጣጫ መከተላችን ኅብረተሰቡ በውኃ ኃብት ልማት
ፕሮጅክቶች ላይ ከማቀድ እስከ ትግበራ ድረስ ተሳታፊ
እንዳይሆን ያደርገዋል፡፡ይህም የባለቤትነት ስሜቱ ዝቅ
148 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !