Page 152 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 152
አብን
አስተዳደር ባለሙያዎችን ማፍራት ላይ ትኩረት አደርጎ
ይሰራል፡፡
በውኃ መሰረተልማቶች ላይ የሚደረግ ኢንቬስትመንትን
በተመለከተ አሁን ያሉት የመጠጥ ውኃ፣ የመስኖ
ፕሮጀክቶችና የውኃ ኃይል ፕሮጀክቶች ጥቂት ናቸው፡፡
ስለዚህ ወጪ ቆጣቢ በሆነ መንገድ አዳዲስ
ፕሮጅክቶችን በመገንባት የሕዝቡን ተጠቃሚነት
ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን አዳዲስ ልማቶች
ለማከናወን የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ከማኅበረሰቡ
መዋጮ፣ ከአበዳሪዎች፣ ተቋማቱን ወደ ግል በማዞር፣
ከውጭ ለጋሾችና ከትረስት ፈንድ ማሰባሰብ ይቻላል፡፡
አብን የሚገነቡ ተቋማትን ዘላቂነት (sustainablity)
በተመለከተ የሚገነቡ የመጠጥ ውኃ ተቋማት ያለባቸው
ትልቁ ችግር ከፍተኛ የሆነ ብልሽትና አገልግሎት
ማቋረጥ፣ ሲበላሹ መለዋወጫ በቀላሉ አለመገኘት
(የአቅርቦትና ሥርጭት ችግር)ን በተመለከተ ለሚገነቡ
ተቋማት በተጠቃሚው ዘንድ የባለቤትነት ስሜት
እንዲዳብር ተቋማቱ የሕብረተሰቡን ፍላጎት መሰረት
ባደረገ አሳታፊ የውኃ ኃብት ልማት አቅጣጫን
ተከትሎ ይሰራል፡፡ እንዲሁም የመለዋወጫ ችግርን
ለመቅረፍ የግል ዘርፉን በመደገፍና በማበረታታት
መለዋወጫዎችን በማምረት ወይም በማቅረብ
እንዲሳተፉ ማደረግ ይገባል፡፡
ተቋማዊ አሰራርንና የውኃ ኃብት አስተዳደር ችግሮችን
በተመለከተ እንደቆሻሻና የበካይ ልቀትን የሚከታተል
ጠንካራ ተቆጣጣሪ አካል አለመኖር፣ በቂ የሕግ፣
150 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !