Page 153 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 153
አብን
የፓሊሲና ስትራቴጅ ማዕቀፍ አለመኖርና ቢኖሩም
በአግባቡ አለመተግበር እንዲሁም የተገነቡ ተቋማትን
በየደረጃው የሚያስተዳድሩ አካላትን ማጠናከርና የገጠሩ
ሕዝብ ድረስ እንዲወርዱ ማድረግ ይገባል፡፡ የውሃ፣
ንጽህናና ጤና ቡድኖችን፣ ውኃ ቦርዶችን የውኃ
አገልግሎት ጽ/ቤቶችን ማጠናከር ያስፈልጋል፡፡
የውኃ ዘርፍ አቅም ግንባታን በተመለከተም የቢሮ
ፋሲሊቲዎች እጥረት፣ የዲዛይንና የኮንስትራክሽን
ጥራት ችግር በተደገጋሚ የሚስተዋሉ ሲሆን እነዚህን
ችግሮች ለመቅረፍ ውጤታማ ዲዛይኖችን ማዘጋጀት
የሚችሉና የተቀናጀ የውኃ ኃብት አስተዳደር እውቀት
ኖሯቸው መስራት የሚችሉ ባለሙያዎችን በሚገባ
ማሰልጠን ይገባል፡፡
በውኃ ልማት ዘርፉ ያለውን የክትትል፣ ግምገማና
ድጋፍን በተመለከተ የውኃ ተቋማት ያሉበት ቦታ፣
ስርጭት፣ የአገልግሎት ሁኔታ፣ ያሉባቸው ችግሮች
ወዘተ ተገቢ የሆነ ቆጠራ አይካሄድም፡፡ ስለዚህ አብን
እነዚህን የውኃ ተቋማት ሁኔታ መረጃ በዘመናዊ
የኢንፎርሜሽን ማኔጅሜንት ሲስተም በመታገዝ
መረጃዎችን የማሰባሰብ፣ የማደራጅትና ለዕቅድና
ክትትል ሥራ ግብዓት እንዲውሉ በማድረግ የሴክተሩን
መረጃ አያያዝ እንዲሻሻል ያደርጋል፡፡
አገራችን ያላት ውስን የውኃ ኃብት ላይ መጠቀም
የሚችለውን የኅብረተሰብ ክፍል ለማሳደግም
በግብርናው ዘርፍ የዘላቂ ውኃ አጠቃቀም
መርኆዎችንና ቴክኖሎጂዎችን (water smart
151 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !