Page 148 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 148

አብን


             ሲሆን  ዓመታዊ  የፍሰት  መጠናቸውም  ወደ  122.8  ቢሊየን

             ኪዩቢክ ሜትር የሚጠጋ ሲሆን የከርሰ ምድር ውኃ አቅሟም
             ወደ 2.6 ቢሊየን ኪዩቢክ ሜትር እንደሚጠጋ ይገመታል፡፡ነገር
             ግን  ይህን  ኃብታችንን  ድህነትን  ለመቀነስና  የሕዝባችን  ኑሮ
             ሊያሻሽል በሚችል ደረጃ እየተጠቀምንበት አይደለም፡፡

             እንደ አማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) እምነት የኢትዮጵያ ውኃ
             ኃብት  ዘርፍ  ልማት  ተቀዳሚና  ዋነኛ  ዓላማው  ሊሆን
             የሚገባው ለዘመናት በኦሪታዊ የድህነት የአኗኗር ዘይቤ እየኖረ

             ውኃ  ከእንሳሳት  ጋር  እየተጋፋ  ከወንዝና  ከምንጭ  ቀድቶ
             ለሚጠጣው  አርሶ  አደርና  በከተማም  የውኃ  ወረፋ  ጥበቃ
             እንቅልፉን  አጥቶ  ሌሊቱን  ሙሉ  ውሃ  ሲጠብቅ  ለሚያድረው
             የከተማ  ነዋሪ  የውኃ  አቅርቦት  ሲቋረጥ  ለ20  ሊትር  ጀሪካን
             ውኃ  20  ብር  እየገዛ  ለሚጠቀመው  የከተሜ  ነዋሪ  ንጹህ
             የመጠጥ  ውኃ  ማቅረብና  የተሻሻለ  የግልና  የአካባቢ  ንጽህና

             አጠባበቅ ተጠቃሚ እንዲሆን ማድረግ አለበት ብሎ ያምናል፡፡
             በዚህ ረገድ ውጤታማ የውኃ ፓሊሲ ለመቅረጽና በአቅርቦትም
             ሆነ በፍላጎቱ ዘርፍ (Supply and Demand management)
             አስፈላጊ      ሥራዎችን          መስራት        ያስፈልጋል፡፡        ከዚህም
             በተጨማሪ  የውኃ  ኃብት  ፓሊሲው  የኢትዮጵያን  ሕዝብ  ኑሮ
             ለመቀየርና  የሥርዓተ-ጾታ  ጉዳይን  ግምት  ውስጥ  በማስገባት
             ሴቶች ለቤተሰባቸው ውኃ ለማቅረብ ያለባቸውን ከፍተኛ ጫና
             ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን መቻል አለበት፡፡ ይህን ለማስቻል

             ደግሞ  የፓሊሲና  የአፈጻጸም  ችግሮች  አስተዋጽኦ  የሚያደርጉ
             ሲሆን      የአማራ       ብሔራዊ        ንቅናቄ(አብን)       የሚከተሉትን
             የፓሊሲና የአሰራር ችግሮች መቀረፍ አለባቸው ብሎ ያምናል፡፡


             146    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   143   144   145   146   147   148   149   150   151   152   153