Page 151 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 151
አብን
ያለ እንዲሆን በማድረግ ዘላቂነታቸው የወረደ እንዲሆን
አድርጎታል፡፡ስለዚህ እንደሌሎች የልማት ፕሮጅቶች
ሁሉ የሚተገበሩ የውኃ ፕሮጅክቶች በሕብረተሰቡ
ፍላጎት ላይ ተመስርተው ከታች ወደ ላይ የልማት
አቅጣጫን ተከትሎ እንዲተገበሩ በማድረግ
የማህኅበረሰቡን የባለቤትነት ስሜት እንዲያዳብር
በማድረግ የሚዘረጉ የውኃ ልማት ተቋማትን
የባለቤትነት ስሜት ለማሳደግ ይሰራል፡፡
የውኃ አስተዳደር ተቋማት ደካማ መሆንና የማስፈጸም
አቅም ውስንነታቸውን ለመቅረፍ የተሻለ የትምህርት
ዝግጅት ያላቸው ባለሙያዎች እንዲቀጠሩና ተቋማቱ
እንዲጠናከሩ ይደረጋል፡፡
የውኃ አስተዳደር ተቋማት በየደረጃው ካሉ ባለድርሻ
አካላት ጋር ያላቸው ግንኙነት የተጠናከረ አለመሆን
እንዲሁም ውኃ ኃብታችንና ተቋማትን የማስተዳደር
ዝቅተኛ እውቀት፣ ክህሎትና አቅም መቀረፍ አለበት፡፡
ለዚህም በውኃ ኃብት አስተዳደርና ውጤታማ
ዲዛይኖችን ማዘጋጀት የሚችሉ ባለሙያዎችን
በጥራትና በበቂ ሁኔታ ማሰልጠን ያስፈልጋል፡፡ በዘርፉ
የሚደረገውን አነስተኛ የምርምርና ልማት በጀት
ማሳደግም ከዚሁ ጋር ተያይዞ መሻሻል ያለበት ጉዳይ
ነው፡፡ ስለዚህ አብን የውኃ አስተዳደር ተቋማትን
የማስፈጸም አቅም እንዲያሻሻል፣ የባለድርሻ አካላት
ግንኙነት እንዲጠናከር፣ እንዲሁም ተገቢውን
እውቀትና ክህሎት ያላቸው የውኃ ኃብት ምህንድስናና
149 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !