Page 147 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 147
አብን
2.6 የውኃ፣ማዕድንና ኢነርጂ ዘርፍ
2.6.1 የውኃ ሐብት ልማትና አካባቢ ጥበቃ
በኢትዮጵያ አሁን ያለው ማኅበረ ኢኮኖሚያዊ ሁኔታ
እንደሚያሳየው የውኃ ኃብቶቻችንና የተፈጥሮ አካባቢያችን
ሰው ሰራሽ ለሆኑ ችግሮች እየተዳረጉ ነው፡፡ከሕዝብ ቁጥር
መጨመርና የከተሞች መስፋፋት ጋር ተያይዞም የውኃ
ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ አድጓል፡፡ ከሕዝብ ብዛት መጨመር
ጎን ለጎን ውኃን በከፍተኛ ሁኔታ የሚፈልጉ የኢኮኖሚ
እንቅስቃሴዎች ማለትም የመስኖ እርሻ፣ የውኃ ኃይል
ማመንጫ፣እንስሳት እርባታ፣ ኢንዱስትሪዎች፣ ቱሪዝም፣
ማዕድን ቁፋሮ፣ የቤት ውስጥ ውኃ ጆታ (ሻዎር፣ሽንት ቤት፣
እቃና ልብስ ማጠቢያ፣ የአትክልት ቦታ ማጠጫና የመኪና
ማጠቢያ ወዘተ…) ማደግ ለውኃ ፍላጎቱ መጨመር
አስተዋጽኦ አድርጓል፡፡ ከውኃ ፍላጎቱ ማደግ ጋር አቅርቦቱም
አብሮ ማደግ ባለመቻሉ አዲስ አበባን ጨምሮ የአገራችን
ከተሞች ከፍተኛ የሆነ የውኃ እጥረት አለባቸው፡፡
በብዙ አካባቢዎች በዝናብ እጥረት፣ ውኃ አጠቃቀም
መጨመርና የውኃ ምንጮችና ተፋሰሶች መድረቅ ያስከተለው
የውኃ እጥረት ደግሞ የምግብ ዋስትናን፣ የኃይል ምርትን፣
የግልና የአካባቢ ንጽህናና ደህንነትን ስጋት ላይ ጥሏል፡፡
በተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎችም የውኃ አጠቃቀም ፉክክሮች
እየጨመሩ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ድንበር ተሸጋሪ
ወንዞችን በአግባቡ የማስተዳደር ችግረም በኢትዮጵያ የውኃ
አስተዳደር ዘርፍ ያለና ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ችግር ነው፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ ከደርዘን በላይ ታላላቅ ወንዞች ያሏት
145 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !