Page 142 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 142

አብን


                          የአካባቢ  እንክብካቤና  ጥበቃ  ኢንተርፕራይዞች

                           (environmental         conservation        and
                           protection      Enterprises)      እንዲቋቋሙና
                           በኢኮኖሚ            እራሳቸውን            እንዲደግፉና
                           አካባቢውንም          እንዲጠብቁና           እንዲንከባከቡ
                           ለማድረግ  የሚያስችል  የማበረታቻ  ሥራዎች
                           ይሰራሉ፡፡  ከፍተኛ  የሆነ  ድጋፍም  ይደረጋል፡፡
                           ይህም የአካባቢውን ማኅበረሰብና ወጣት ባማከለ
                           መልኩ እንዲተገበር ይደረጋል፡፡

                          በመዳረሻዎች  አካባቢ  የሚለሙ  የቱሪዝምና
                           ሆቴል  እንዲሁም  ሌሎች  የኢንቨስትመንት
                           ሥራዎች የቆሻሻ አወጋገድ ስርዓትና የማጣራት
                           ደረጃ  ዓለምአቀፍ  ደረጃውን  በጠበቀ  መልኩ
                           እንዲዘጋጅና ተፈፃሚ እንዲሆን ይሰራል፡፡ የሕግ
                           ማዕቀፍም ይዘጋጅለታል፡፡

                          የጥብቅ       ስፍራዎች        እንክብካቤና        የቅርሶች
                           እድሳት የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶት የሚሰራ
                           ሥራ ይሆናል፡፡


                        ሠ. የዱር እንስሳትና ኢኮ-ቱሪዝም
             ኢትዮጵያ  በተፈጥሮ  ኃብት  ከታደሉት  አገራት  በግንባር
             ቀደምትነት  የሚትጠቀስ  ናት፡፡              ከባሕላዊና  ታሪካዊ  ቅርሶች

             በተጨማሪ  የተለያዩ  ጥብቅ  ክልሎች፣  ብሔራዊ  ፓርኮች፣
             የተፈጥሮ ደኖች፣ ኃይቆችና ወንዞች ባለቤትም ናት፡፡



             140    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   137   138   139   140   141   142   143   144   145   146   147