Page 139 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 139

አብን


                      አገርም እንዲያለማ ሰፊ ድጋፍና ርብርብ ይደረጋል፡፡

                      ይህም  ትልቅ  የእውቀትና  ልምድ  ተሞክሮን  በአገር
                      ውስጥ       ለማስፋፋት        ሰፊ     ሚና      እንደሚኖረው
                      ይታመናል፡፡

                     የዓለምአቀፍ  ተቋማት  የኮከብ  ደረጃ  ምደባ  መመዘኛ
                      እንዳለ  ሆኖ  ከዛ  በታች  የሆኑትን  ተቋማት  አቅምና
                      ጥራት  ለማሳደግ  በሕግና  መመሪያ  የታቀፈ  ድጋፍ
                      ክትትልና        ቁጥጥር       ይደረጋል፡፡የደረጃ         መመዘኛ

                      መስፈርቶችን  በማውጣት  ክልላዊና  አካባቢያዊ  ደረጃ
                      የማውጣትና  ደረጃ  የመመደብ  ሥራ  እንዲሰራ
                      ይደረጋል፡፡




                        ሐ.  የኅብረተሰብ  ተጠቃሚነትና  የማኅበረሰብ  አቀፍ
                        ልማት ስርፀትን በተመለከተ

             ሕብረተሰቡ  የበይ  ተመልካች  ብቻ  ሳይሆን  የልማቱ  እኩልና
             ፍትኃዊ ተቋዳሽ እንዲሆን ለማድረግ፡-

                      በቱሪስት        መዳረሻዎችና           የቱሪስት        መስህብ
                        ስፈራዎች  አካባቢ  ያለው  የኅብረተስብ  ክፍል  ንቁ

                        ተሳታፊ  እንዲሆን  የማነቃቃት፣  የማስተማርና
                        የማሳተፍ ሥራ ይሰራል፡፡




             137    ጊዜው አሁን ነው!                        አብንን ይምረጡ !
   134   135   136   137   138   139   140   141   142   143   144