Page 143 - የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) የምርጫ ማኒፌስቶ
P. 143
አብን
በመሆኑም አብን ቀጣይነት ያለው ጥቅም እንድሰጡ
የሚከተሉት የፖሊሲ አቅጣጫዎች ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
የአካባቢውን ማኅበረሰብ የኃብቱ ባለቤትነት
እንዲሰማው ማድረግ፣በትኩረት መጠበቅና
መቆጣጠር እንድችል ማበረታታት፣ ኃላፊነት
እንዲሰማው ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና
መስጠት፣ በማንኛውም ሁኔታ ማሳተፍ
(ኃላፊነት የሚሰማው ትውልድ መፍጠር)
የሚመለከታቸው አካላት በጋራና በተቀናጀ
ሁኔታ መስራት (የግብርና ባለሙያ፣
የቱሪዝም፣ የአፈርና ውኃ ጥበቃ፣ የዱር
እንስሳት፣ የደን ባለሙያ፣ ወዘተ) በተፈጥሮ
ጥብቅ ቦታዎች፣ በታሪካዊና ባሕላዊ ቦታዎች፣
በኃይቆችና ወንዞች ዙሪያ በጋራና በዘላቂነት
መስራት
ለአካባቢው ማኅበረሰብ ከቱሪስት ገቢ የተወሰነ
ፐርሰንት (15%) እንድጠቀም ማድረግ፣
በተጨማሪም ዘላቂነት ያለው የገቢ ማጠናከሪያ
መስጠት (የቴክኖሎጅ ሽግግር፣ ምር ጥዘር፣) ፣
ወጣቶችን ማደራጀትና ሙያዊ ስልጠና
መስጠት (ቱርጋይድ፣ የሆቴል ሥራ፣ለቱሪስት
የሚሸጡና የሚከራዩ ዕቃዎችን ማምረት) ፤
የአካባቢ ጥበቃና (Rehabilitation) ማጠናከር፣
በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን ማደራጀት፣መደገፍ
እንድሁም ልዩ ልዩ ክለቦችን ማቋቋምና
141 ጊዜው አሁን ነው! አብንን ይምረጡ !