Page 4 - በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ የግብርና ሚኒስቴር የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና
P. 4
ኒ
ር ሚ
ስ
ክቡ
የ የክቡር ሚኒስትር ዴኤታ መልዕከት
ኤ
ር ዴ
ታ መል
ከ
ዕ
ት
ት
የግብርና ሴክተሩ የእርሻ፤ የተፈጥሮ፤ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፎችን በማሳደግ፣ የኤክስፖርት
ሰብሎችን አማራጭ ለማስፋት፣ ከውጭ የሚገቡትን ምርቶች በሀገር ውስጥ ምርቶች ለመተካት፣ ለአግሮ
ኢንደስትሪ በጥራትና በበቂ መጠን የጥሬ ዕቃ ለማቅረብና የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ
በሚደረገው ርብርብ ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር ምርትና
ምርታማነት ከማሳደግ አንፃር ሰፋፊ ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም ከአገሪቱ የህዝብ እድገት ጋር ሲነጻጸር
ያነሰ በመሆኑ የህዝቡን ምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አንጻር ውስንነት አለበት፡፡
ይህን ስር የሰደደ ችግር ለመቅረፍ የምግብ ሥርዓትን ማዕከል ያደረገ የግብርና መር አሰራር (Agri-
Food System) አዋጭና ዘላቂ የሆነ አካሄድ መሆኑ ይታወቀል፡፡ ግብርና ሚኒስቴርም በተሰጠው ተግባርና
ኃላፊነት መሰረት ስርዓተ ምግብ ተኮር የአመራረትና የአመጋገብ ስርዓትን በመዘርጋት የተለያዩ በምግብ
ንጥረ ነገር የበለጸጉ የሰብል ዝርያዎችን በግብርና ምርምር ማዕከላት እንዲፈልቁና በአርሶ/አርብቶ አደሮች
ዘንድ እንዲተዋወቁ በማድረግ ወደ ምርት ስርዓት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ እነዚህ በምግብ ንጥረ ነገር
ይዘታቸው የበለጸጉ የኬናዋ፣ የካሚሊ እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) ሰብሎች ለሀገራችን አርሶ አደሮችና
ባለሙያዎች አዲስ እንደመሆናቸው የአመራረት እና አጠቃቀም ማኑዋሎች ተዘጋቶላቸዋል፡፡ የተዘጋጁት
ማኑዋሎች የተሻሻለ የአመራረት ስርዓት እንዲዘረጋ ሚናቸው የጎላ ነው፡፡ ስለሆነም ማኑዋሎቹ በፌደራል፣
በክልል እና በወረዳ ደረጃ በሰብል ልማት፣ በሰብል ጥበቃ፣ በግብርና ኤክስቴንሽን፣ በእሴት ጭመራ እና
በስርዓተ ምግብ ዋስትና ሥራ ላይ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እንደ መመሪያ እንዲጠቀሙበት እንዲሁም
ለፖሊሲ አውጭዎች፣ ለተመራማሪዎች፣ ለሌሎች ሙያተኞች እና ለስቪክ ማህበረሰቡ እንደ ማጣቀሻ
እንዲገለገሉበት እመክራለሁ፡፡ በመጨረሻም ይህንን ሰነድ በማዘጋጀት በኩል አስተዋጽ ላደረጉ የግብርና
ሚኒስቴር፤ ምርምር ማዕከላት፤ ዳን ቸርች ኤድ እና የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡
ዶ/ር መለስ መኮንን
የእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ
የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል የኬነዋ፣ የካሚሊና እና የምግብ ሲናር (ኦትስ) አመራረትና አጠቃቀም ማኑዋል