Page 89 - Dinq Magazine July 2020
P. 89

መጪውን ዘመን መተንበይ የሚፈልጉ ሰዎች ካሉ፤ በሰኔ እና ሰኞ
        ግጥምጥም አመታት ላይ፤ የከዋክብትን ስነ ፈለጋዊ እውቀት ጋር ቢያ
        ቀናጁት የተሻለ ውጤት ሊያገኙ ይችላሉ። ከጊዜ በኋላ የስነ ከዋክብት
        እውቀት እየደበዘዘ በመምጣቱ እንጂ፤ ከባቢሎን ዘመን በፊት ጀምሮ፤
        ሊቃውንት እቀት እና ጊዜያቸውን በከዋክብት ቀመር ላይ ያጠፉ ነበር።
        በውጤቱም  በአገራቸው  ላይ  ሊመጣ  የሚችለውን  የረሃብ፣  የበሽታ፣
        የድርቅ እና የጦርነት ዘመን ቀድመው መተንበይ እና መናገር ይችሉ
        ነበር። ጥሩ ምርት የሚገኝበትን ተድላ እና ሃሴት የሚሆንበትን፣ ታዋቂ
        ሰዎች እና ነገስታት የሚሞቱበትን፤ ያንን ተከትሎ የሚመጣውን ውጣ
        ውረድ ጭምር ይናገራሉ፤ ማስጠንቀቂያም ይሰጣሉ። እውቀቱ አሁንም
        አለ።

            ለማንኛውም ከዚህ በታች ሰኔ እና ሰኞ የሚገጥምባቸውን አመተ
        ምህረቶች አስቀምጠናል (ሁሉም በፈረንጅ አቆጣጠር ነው) ትንቢት
        መናገር  የሚፈልጉ  ካሉ፤  በነዚህ  አመታት  የከዋክብትን  ተፅእኖ
        (ማለትም መጪው ጊዜ፣ የጦርነት፣ የረሃብ፣ የበሽታ) መሆኑን በመ
        ተንበይ፤ ጸሎት እና ምህላ የሚያስፈልግበት ዘመን ካለም፤ ሁሉም እን
        ደየእምነቱ ወደፈጣሪው ኤሎሄ የሚልበትን ወቅት ሊነግሩን ይችላሉ።
        ከዚህ በታች ያሉት አመታት ሰኔና ሰኞ የሚገጥምባቸው ናቸው።

            2026፣  2037፣  2043፣  2048፣  2054፣  2065፣
        2071፣ 2076፣ 2082፣ 2093፣ 2099 - በየ11 አመት
        በሚመጣው የአበቅቴ ጥሎሽ ወይም በሰኔ እና ሰኞ ግጥምጥሞሽ ማመን
        ወይም አለማመን የግል ምርጫ ነው። እኛ ግን እንላለን 2026 እስ
        ከሚመጣ ድረስ… መጪው ዘመን የሰላም ይሁንልን።


              DINQ    magazine   July   2020   #210                                               happy   independence   day                                                                                                                                                  Page 89
   84   85   86   87   88   89   90   91   92   93   94