Page 4 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 4

የክቡር ሚ ኒስትር ዴኤ ታ መልዕ ከት
                                የክቡር ሚኒስትር ዴኤታ መልዕከት


        የግብርና ሴክተሩ የእርሻ፤ የተፈጥሮ፤ የእንስሳትና ዓሳ ሃብት ልማት ዘርፎችን በማሳደግ፣ የኤክስፖርት ሰብሎችን
        አማራጭ  ለማስፋት፣  ከውጭ  የሚገቡትን  ምርቶች  በሀገር  ውስጥ  ምርቶች  ለመተካት፣  ለአግሮ  ኢንደስትሪ
        በጥራትና በበቂ መጠን የጥሬ ዕቃ ለማቅረብና የምግብና ስርዓተ ምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ በሚደረገው ርብርብ

        ላይ ከፍተኛ ሚና እየተጫወተ ይገኛል፡፡ ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር ምርትና ምርታማነት ከማሳደግ አንፃር ሰፋፊ
        ውጤቶች የተመዘገቡ ቢሆንም ከአገሪቱ የህዝብ እድገት ጋር ሲነጻጸር ያነሰ በመሆኑ የህዝቡን ምግብና ስርዓተ
        ምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ አንጻር ውስንነት አለበት፡፡



        ይህን ስር የሰደደ ችግር ለመቅረፍ የምግብ ሥርዓትን ማዕከል ያደረገ የግብርና መር አሰራር (Agri-Food System)
        አዋጭና ዘላቂ የሆነ አካሄድ መሆኑ ይታወቀል፡፡ ግብርና ሚኒስቴርም በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት

        ስርዓተ ምግብ ተኮር የአመራረትና የአመጋገብ ስርዓትን በመዘርጋት የተለያዩ በምግብ ንጥረ ነገር የበለጸጉ የሰብል
        ዝርያዎችን በግብርና ምርምር ማዕከላት እንዲፈልቁና  በአርሶ/አርብቶ አደሮች ዘንድ እንዲተዋወቁ በማድረግ ወደ
        ምርት ስርዓት እንዲገቡ ተደርጓል፡፡ ይህ የአሉማ ሰብል በምግብ ንጥረ ነገር ይዘቱ የበለጸገ ሰብል ሲሆን ለሀገራችን

        አርሶ አደሮችና ባለሙያዎች አዲስ እንደመሆኑ የአመራረት እና የአጠቃቀም ፓኬጅ ተዘጋጅቶለታል፡፡ የተዘጋጀው
        ፓኬጅ የተሻሻለ የአመራረት ስርዓት እንዲዘረጋ ሚናው የጎላ ነው፡፡ ስለሆነም ፓኬጁ  በፌደራል፣ በክልል እና
        በወረዳ ደረጃ በሰብል ልማት፣ በሰብል ጥበቃ፣ በግብርና ኤክስቴንሽን፣ በእሴት ጭመራ እና በስርዓተ ምግብ

        ዋስትና ሥራ ላይ ለተሰማሩ ባለድርሻ አካላት እንደ መመሪያ እንዲጠቀሙበት እንዲሁም ለፖሊሲ አውጭዎች፣
        ለተመራማሪዎች፣ ለሌሎች ሙያተኞች እና ለስቪክ ማህበረሰቡ እንደ ማጣቀሻ እንዲገለገሉበት እመክራለሁ፡፡
        በመጨረሻም ይህንን ሰነድ በማዘጋጀት በኩል አስተዋጽ ላደረጉ የግብርና ሚኒስቴርና ምርምር ማዕከላት ላቅ ያለ

        ምስጋናዬን አቀርባለሁ፡፡


        ዶ/ር መለስ መኮንን







        የእርሻ ልማት ዘርፍ ሚኒስቴር ዴኤታ
   1   2   3   4   5   6   7   8   9