Page 7 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 7
1
መግቢያ
1. 1. መግቢያ
አሉማ የAmaranthaceae ቤተሰብ ውስጥ የሚመደብ ሲሆን ከ 60- 70 የተለያዩ አይነቴዎች (species)
ይገኛሉ፡፡ የአሉማ ሰብል ምንም እንኳን በደቡብ አሜሪካ የተገኘ ቢሆንም በአብዛኛዎቹ የአለም ሀገራት ፍሬውና
ቅጠሉ ለምግብነት ይውላል፡፡ በኡጋንዳ እና ካሜሩን በስፋት በመመረት ቅጠሉ ለምግብነት የሚውል ሲሆን
በተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ጎረቤት ኬንያን ጨምሮ ጥቅም ላይ ይውላል። አንዳንድ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት
ይህ ሰብል በሀገራችን በምእራብና በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ በስፋት የሚመረት ቢሆንም እንደ ሌሎች ሰብሎች
ተዘርቶ የሚሰበሰብ ሳይሆን፤ ከመጀመሪያው ዝናብ በኋላ በአፈር ውስጥ የሚገኘው የአሉማ ዘር በራሱ የሚበቅል
ሲሆን የምግብ እጥረት በሚኖርበት ወቅት ተሰብስቦ ለምግብነት ይውላል፡፡ የአሉማ ሰብል መጠሪያ ስሙ
በሀገራችን የተለያዩ አከባቢዎች የሚለያይ ሲሆን በአማርኛ አሉማ፣ ሊሻልሾ፣ የፈረንጅ ጤፍ፤ በኦሮምኛ ሰመሌ፣
እያሶ፣ ጆሊሊ እና በትግርኛ ሀምሊ ጥሊያን፤ በወላይታ ገገብሳ በመባል ይታወቃል።
የአሉማ ሰብል ቀደምት ከሆኑ የሰብል አይነቶች አንዱ ሲሆን በዓለም ዙሪያ የምግብ እና ስርዓት ምግብ ዋስትናን
ለማረጋገጥ ጉልህ አስተዋፅኦ እያደረገ የሚገኝ ሰብል ነው፡፡ ይህ ሰብል ለዘመናት ከእርሻ የጠፋና በአሁኑ ወቅት
በተለያዩ ሀገራት የሚመረትና ቅጠሉ እንደ አትክልት፣ ፍሬው/ዘሩ ደግሞ እንደ እህል ሰብል በተለያየ መልኩ ጥቅም
ላይ ከመዋሉ ባሻገር ምቹ ባልሆኑ የአየር ንብረት ሁኔታዎችና አካባቢዎች የማደግ ችሎታ ያለው በመሆኑ የምግብና
ስርዓተ-ምግብ ዋስትናን በቤተሰብ ደረጃ ለማረጋገጥ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡
የአሉማ አትክልት (ቅጠሉ) በተለያዩ ሀገራት እንደምግብ አዘገጃጀት ልምድ የሚለያይ ሲሆን በጎመን መልክ፣
በሰላጣ፣ በሾርባ እና በተለያየ መልኩ በማዘጋጀት ለምግብነት ይውላል:፡በተጨማሪም ግንድ እና የቆዩ ቅጠሎች
ለከብቶች መኖነት፣ እህሉ (grain) ደግሞ ተፈጭቶ እንደ ስንዴ፣ በቆሎና ገብስ ከመሳሰሉ የምግብ ሰብሎች ጋር
ተደባልቆ ለምግብነት ይውላል:፡በመሆኑም በተለያዩ ሬሾዎች/ድርሻዎች የአሉማ እና የሌሎች እህሎች ዱቄቶች
ውህድን በመጠቀም ለቂጣ፣ ለዳቦ፣ ገንፎ፣ ለብስኩት፣ ሳንቡሳ፣ ዶናት፣ ኬኮች እና ሌሎች ምግቦችን በቤት
ውስጥ ለማዘጋጀት ያገለግላል። የአሉማ ዱቄት ብቻውን ገንፎን ለማዘጋጀት ያገለግላል። በሀገራችን አንዳንድ
አከባቢዎች ቅጠሉን እንደ ጎመን በመቀቀል እና ፍሬውን ከሌሎች ሰብሎች ጋር በማደባለቅ ለምግብነት ጥቅም
ላይ ያውሉታል፡፡
እንዲሁም አሉማ በምግብ ንጥረ ነገሮች ይዘቱ የታወቀ ሲሆን በቅጠሉ ውስጥ የተለያዩ ቫይታሚኖች (ኤ፣ ኬ፣
ቢ6፣ ሲ)፣ ራይቦፍላቪን እና ፎሌት የበለፀገ ከመሆኑም በላይ እንደ ካልሲየም፣ ብረት፣ ማግኒዥየም፣ ፎስፈረስ፣
ጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ