Page 11 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 11
5
ተ. ቁ የዝርያው ተስማሚ የዝናብ የመድረሻ የቅጠሉ ምርታማነት የተለቀቀበት መስራች
ስም ከፍታ መጠን ጊዜ ቀለም ኩ/ሄክታር ዓ. ም ዘር አራቢ
(ሜ) (ሚ.ሜ) (ቀናት) ማዕከል
በምርምር በአርሶ
ማሳ አደር
ማሳ
1 ማዲራ-II 1550- 800-1300 4-5 አረንጓዴ 140-160 - 2018 G.C መልካሳ
(Madii- 2400 ሳምንታት ግብርና
ra-II) ምርምር
ማዕከል
2 AC-NL 1550- 800-1300 4-5 ›› 150-175 - 2018 G.C ››
2400 ሳምንታት
ምንጭ፡ ግብርና ሚ/ር, 2018 G.C
3.3. የዘር ወቅት
3.3. የዘር ወቅት
የአሉማ ሰብል በመኸርም ሆነ በበልግ ልክ ዝናብ ሲጀምር ሊዘራ ይችላል፡፡ በተጨማሪም በደጋፊ መስኖ ሊመረት
የሚችልና በአንጻራዊ ሁኔታ ድርቅን በመቋቋም በቂ ምርት መስጠት ይችላል። ሰብሉ የውሀ እጥረት በሚያጋጥመው
ወቅት እርጥበት እስኪያገኝ እድገቱን ይገታል። ሆኖም ደጋፊ መስኖ ከተጠቀምን እድገቱ ቀጥሎ ምርት ይሰጣል፡፡
3.4. የዘር መጠንና አዘራር
3.4. የዘር መጠንና አዘራር
የአሉማ ሰብልን ለማምረት የሚያስፈልገው የዘር መጠን እንደ አመራረት አይነቱ የሚለያይ ሲሆን ዘሩን በቀጥታ
በመስመር እና በብተና ወይም ችግኝ በማፍላት (በመደብ/ትሬይ) እና በደንብ በተዘጋጀ ማሳ ላይ በማዛወር
ማምረት ይቻላል፡፡ በቀጥታ በዋናው ማሳ ላይ ሲዘራ (direct sowing) በሄክታር እስከ 2.70 ኪ. ግራም ዘር
ሊያስፈልግ ይችላል። የሰብሉ ዘር መጠን በጣም ትንሽ (tiny) በመሆኑ የመዝራት ሂደቱን ለማቀላጠፍና በተክል
መካከል ያለውን ርቀት የተስተካከለ እንዲሆን ይረዳ ዘንድ አንድ እጅ ዘር ከአስር እጅ አሸዋ ጋር በአግባቡ በመቀየጥ
መዝራት ያስፈልጋል፡፡
በአንድ ጊዜ ነቅሎ ምርት ለመሰብሰብ ዘሩን በመስመር መካከል 10 ሳ.ሜ እና በተክሎች መካከል 5 ሳ.ሜ በማራራቅ
በመዝራት አፈር በስሱ መሸፈን ያስፈልጋል፡፡ ነገር ግን ማሳው ላይ ቆይቶ በተደጋጋሚ ምርት ለመሰብስብ ሰፋ ያለ
ቦታ ስለሚያስፈልገው፤ በመስመር መካከል 20 ሳ.ሜ እና ተክሎች መካከል 20 ሳ.ሜ የመዝሪያ ርቀት መጠቀም
ለዝናብ ወቅት ሲያገለግል፤ በመስኖ ወቅት ደግሞ 40 ሳ.ሜ በመስመር እና 20 ሳ.ሜ በተክሎች መካከል መጠቀም
ጅ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ
የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ