Page 14 - Aluma-Amaranthus for design 26.04.14
P. 14

8
        የምርት መጠኑን ይጨምራል።



           ሰብል
        4.  4.  ሰብል ጥበቃ
               ጥበቃ
          4.1.
               አረም

                    ቁጥጥር
          4.1.     አረም ቁጥጥር
        አረሞች በአሉማ ምርትና ጥራት ላይ ተጽእኖ ይፈጥራሉ። አሉማ የመጀመሪያዎቹ የዕድገት ወቅት በዝግታ የሚያድግ
        ሰብል በመሆኑ በተለያዩ አረሞች ይጠቃል:: አረም ከተከላ በፊት ቀደምት አረምን በማረስ ወይም በታወቀ የአረም
        ማጥፊያ ኬሚካል ቁጥጥር ሊደረግለት ይገባል። ስለዚህ  በዚህ ወቅት የሚወጡ አረሞችን ለመቆጣጠር ሶስት ወይም
        አራት እርሻዎች ሊያስፈልጉ ይችላሉ። ሰብሉ በፍጥነት ማደግ ሲጀምር፤ የሰብሉ ጥላ ዘግይቶ ከሚበቅለው አረም

        ሊበልጥ ስለሚችል አረሙ በሰብሉ ላይ ያለው ተፅዕኖ ኢምንት ሊሆን ይችላል። እንዲሁም ሰብሉ በመጀመሪያዎቹ
        እድገት ደረጃ ከሌሎች አረሞች ጋር ስለሚመሳሰል ዘሩን በመስመር በመዝራት ከመስመር ውጭ የበቀሉትን አረሞች
        በመንቀል መከላከል ይቻላል፡፡


          4.2.    የበሽ ታና   ተባይ   ቁጥጥር
          4.2.  የበሽታና ተባይ ቁጥጥር
        በአመራረት ጊዜ ጉልህ የሆኑ የበሽታ ችግር የቅጠል አሉማ ላይ አይታወቅም። የተለመደው የበሽታ ችግር በችግኝ

        ደረጃ እርጥበት ሲበዛ ችግኞችን ሊገድል የሚችል አፈር ወይም ዘር ወለድ ፈንገስ የዳምፒንግኦፍ (damping off)
        በሽታ ያስከትላል። ስለዚህ ከበሽታ ነፃ የሆኑ ዘሮችን መጠቀም፣ ከመጠን በላይ ውሃ መጠቀምንና እና ጥቅጥቅ ያለ
        ተከላን ማስወገድ ያስፈልጋል።


        የተለያዩ የተባይ አይነቶች ቅጠሉን፣ ግንዱን እና አበባውን ያጠቃሉ፡፡ ለምሳሌ በሌሎች ሀገራት እንደተመለከተው
        ቅጠል የሚሰረስሩ ተባዮች (leaf miner)፤ ክሽክሽ (aphids)፣ ጓያ ትል (ball worm)፣ ነቀዝ (weevil)፣ ቀይ

        ሸረሪት  (Red  spider  mite)  እና  ሌሎች  አልፎ  አልፎ  የሚከሰቱ  (sporadic  insects)  ቅጠሉን፣  ግንዱንና
        አበባውን የሚያጠቁ ተባዮች ይገኙበታል፡፡ በእኛ ሀገር የተለመደው ቅጠል አሉማን የሚያጠቃው ተባይ፤ ቆራጭ

        ትል (caterpillar) ሲሆን ቅጠሉን በመበጣጠስ ምርትና ጥራቱን ይቀንሳል። እጮቹ (በትል ደርጃ) ቅጠሎችን
        አጽም እስከሚሆኑ ድረስ ይመገባሉ። የተባዩን ጉዳት ለመቀነስ በተባዩ የተጎዱ ቅጠሎችን ሰብስቦ ማስወገድ አንዱ
        መከላከያ መንገድ ሲሆን እንደ ጉዳት መጠኑ አይቶ ባለሙያ በማማከር ለዚሁ ተባይ መቆጣጠሪያ የሚመከረውን

        እንደ ካራቲንና ትሬሰር ያሉ ተባይ መቆጣጠሪያ መድሀኒቶችን መጠቀም ይቻላል።






                                                                             ጅ
                                           የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬጅ
                                           የአሉማ (Amaranthus spp.) ሰብል አመራረት እና አጠቃቀም ፓኬ
   9   10   11   12   13   14   15   16   17   18   19